ስህተትን ማመን ለመጪው ድል ዋስትና ነው

 

ከፍኖተ ዴሞክራሲ ሊነበብ የሚገባ ወቅታዊ ሐተታ፡ ወያኔ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ የተቃዋሚው ጎራ አያሌ ስህተቶችን እየፈጸመ በራሱ ላይ ቀንበርን ጭኗል።  ይህን መካድ አይቻልም። ጊዜውን ስንቃኝ፣ የፈጸምነውን ስህተት መረዳት እንችላለን — ባዕዳንና ወያኔ ከፈጸሙብን ጥቃት ባልተናነሰ የራሳችን መሪ ተብዬዎች፤ ዶክተር አቃፊ፣ ኢንጂነር ነን ባዮች የፈፀሙት ስህተትና በደል ልክ የለውም። ዋናው ጥፋት ግን ስህተትን ለማረም ድፍረት ማጣቱ ነው።  ሀገርና ትውልድን ያጠፋውን ፈርጣጭ ግለሰብ መድረክ ሰጥተው የሚያዳንቁ አጠፋችሁ ሲባሉ አዎ ተሳስተን ነበር ማለቱ አቅቷቸውል። ሀገርን እያጠፋ ካለው ሀያል መንግስት ስር የወደቁ ከትቢያው አንነሳ ብለው እስካሁን አሉ።  ሕዝብን እንደ ዕቃ የሸጡ ሀገር ወዳድ ተብለው መድረክ እየተሰጣቸው ነው።  ታዲያ የራሳችን ጠላት ራሳችን ነን ቢባል ምን ስህተት አለው?  ሙሉውን ጽሑፍ ያንብቡ…