አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ!

(ዴሞ፣ ቅጽ  44፣ ቁ . 2፣ ጥቅምት/ኅዳር 2011) – ዛሬ በሀገራችን፣ ወደ ኋላ  ሊቀለበስ የማይችል በሕዝብ አመጽ የሚካሄድ ለውጥ አለ።  የለውጡ መዳረሻ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲሆን ሁሉም ዜጋ ጓጎቶ ይጠብቃል።  እንደሚሳክም ያምንበታል።  የለውጡ አቅጣጫና አካሄድ ምን ሳንካ ያጋጥመው ይሆን በማለት በሥጋትና በተመስጦ የሚከታተሉ አያሌ ወገኖች አሉ።  የመጀመሪያው ባለጉዳይ ለውጡን በትግሉ ያስገኘው፤ አመፀኛው ያው ራሱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመሆኑ አጠራጣሪ አይሆንም።  ለውጡ ሳንካ ገጥሞት ተንገራግጮ እንዲሰናከል የማይፈልገው ሕዝብ፤  ላስገኘው ለውጥ ቀናዒ ነው።  ሁለተኛው ለአለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት የኢትዮጵያን ሕዝብ ጨቁኖ በመግዛት ሀብቷን ሲመዘብርና ንብረቷን ሲያሸሸ የነበረው ወያኔና ተባባሪው ክፍል ደግሞ የነበረውን ጥቅም ለማቆየት ሲል ለውጡ እንዲሰናከልለት ይመኛል።  በሦስተኛ ደረጃ፡ ኢትዮጵያን ከዕይታው ጨርሶ ሊያወጣት የማይፈለገው የውጭ ኃይል ነው።  የውጭው ባዕድ ኃይል፣  በሀገሪቱ ላይ ሥልጣን የሚይዘውን ማንኛውንም መንግሥት፤ በሆነው ዘዴ የመቆጣጠር ኃይል እስካላገኘ ድረስ፤ ተንኮል ከመሸረብ ፈፅሞ አይተኛም። ለዚህም ቅጥረኞች አያጣም።  ሙሉውን  እትም ያንብቡ . . . .