የምርጫ ቧልት አባዜ

ዴሞ (የኢሕአፓ ልሳን) – ለግማሽ ምዕተ ዓመት ያህል ሕዝብ የሥልጣን ምንጭ የሚሆንበትን ሥርዓት እውን እንዲሆን ሲካሄድ የነበረውና ኢትዮጵያውያን እስከዳር የተሳፉበት ሕዝባዊ ትግል ላለፉት እነዚህ ዓመታት የእልህ አስጨራሽ ጉዞ ያለማቋረጥ ቢያደርግም እስካሁን በድል ሊጠናቀቅ አለመቻሉ ግልጽ ነው። ኢሕአፓ ልሳኑ በሆነው ዴሞክራሲያ፥ በተለያዩ የዘወትር መጣጥፎቹና በሌሎችም የመገናኛ ዘዴዎቹ፣ የሕዝባዊ ትግል ግብ የሆነው የሥርዓት ለውጥ እውን ያልሆነባቸውን ምክንያቶች በየምዕራፉ ሲዘረዝር፣ ሲተነትንና ሲጠቁም፣ አደጋዎችን ሲያስገነዝብና አቅጣጫንም ሲያመላክት መቆየቱም ይታወቃል። ቀደም ብሎ በተሰራጩት የዴሞክራሲያዊ እትሞች የተስተናገዱት ጉዳዮች እንደተጠበቁ ሆነው በአሁኑ ወቅት አገራችን ያለችበትን ሁኔታ ድርጅታችን ኢሕአፓ እንዴት ያየዋል? ዋና ዋና ችግሮቹስ ምንድናቸው? ችግሮቹንስ ለማስወገድ የሚረዱ እርምጃዎችስ ምን ሊሆኑ ይገባል? የሚሉትንና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችን በዚህ የዴሞክራሲያ እትም እናነሳለን፡፡ ሙሉውን እትም ያንብቡ