የወደቀን አንሳ፤ የሞተን አትርሳ

ከፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ  አንድነት ድምጽ  – ሰማዕቱን የማይረሳ፤ የወደቁትን የሚያነሳ ትውልድ የምታፈራ ሀገር ምንኛ የተደለች ነች? ኢትዮጵያ ሀገራችንስ ይህ ዕድል አለኝ ብላ ትፅናናለች እንዴ?  ወይስ ዕድሉ እንዲኖራት ትመኛለች?  ሰማዕታቱ ተረስተው፤ ዐርበኞቿ ተዋርደው፤ ታስረው፤ በዐደባባይዋ ተሰቅለው፤ ቤተዘመዶቻቸው ተብትነው መቅረታቸውን ነው?   ወይስ አይ፤ ይህ ሁሉ አልተፈፀመም ብላ በዕርግጠኘነት ልትናገር ትችላለች?   እንደ ድመት፤ የራሷን ልጆች ትበላለች?  ወይስ፤ ልጆቿን ከአጥፊዎች ታድናለች?    የሞተላት ፆም አድሮ፤ የገደላት – የከዳት ተንቀባርሮ፤  የአመናት – ያፈቀራት አንገቱን ቀብሮ፤  ሌባ – ቀጣፊው ሀብቷን ዘርፎ፤ የሚኮበልልባት ሀገር ነች?   ወይስ አይደለችም?   ለእነኝህና  ለተመሳሳይ ጥያቄዎች  ትክክለኛውን መልስ ልትሰጥ የምትችል ራሷ ሀገራችን  ነች።   “ሰው ሞኝ አንድ እንጭት ያስራል”   እንደሚባለው ተረት፤ ሀገሪቱ ግዑዝ ስለሆነች፤  እርሷ ልትጠየቅ አይገባትም ሊባል ይቻል ይሆናል።  በሌላ  በኩል ደግሞ፤  የልጆቿን  ደህንነት  ባለመጠበቋ ግን፤ በኃላፊነት ከመጠየቅ አታመልጥም የሚሉ ዜጎቿ ቁጥር ቀላል አይደለም።  እንዲያውም ከዚህ አልፈው – ተርፈው፤  ሀገራችን በድላናለች ብለው በፍርድ ቤት ለመክሰስ የሚያስቡ እንዳሉ ተደጋግሞ  ይሰማል፡፡   በዚህ ፋይል ተከፍቶባት ብትከሰስ፤ ጠበቃ የሚቆምላት ማን ይሆናል?   ጉዳዩ  የኅሊና  ጥያቄም ጭምር በመሆኑ፤ ሁሉም ዜጎቿ ሊያስቡበት ይገባል! . . .  መላውን  ሀተታ ያንብቡ