የወባ በሽታ ወደ ደጋማ ቦታዎች እየተሰራጨ ነው

ዜናና ኃተታ (ሰኔ 10 ቀን 2009 ዓ.ም.) – የወባ በሽታ ወደ ደጋማ ቦታዎች እየተሰራጨ ነው – ከጂቡቲና ከኤርትራ ወሰን የካታር ሲነሳ ሻዕቢያ ወታደሮቹን አሰማራ – አንዳንድ የተቃዋሚ ድርጅት ነን የሚሉ በአስመራ ለማካሄድ ያቀዱት ስብሰባ ተወገዘ – በሊቢያው መአመር ጋዳፊ ላይ…

የሞራል ጥያቄ

የፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሀተታ- የሰውን ልጅ፤ ህይወት ካላቸው ከሌሎች ተንቀሳቃሽ ፍጡራን የተለየ ከሚያደርገው አንዱ፤የሞራል ጥያቄ ነው። ይህ የሞራል ጥያቄ ፤ የሰውን ልጅ በመሠረቱ ከእንስሳት ይለየዋል መባሉ፤ እንስሳቱና አራዊቱ እንደሚኖርቱ የዘፈቀደ ህይወት ለመምራት አለመፈለጉ ነው። ሰውን ሰው ሊያደርጉት ከሚችሉት…

ህዝባዊ አመጽ ዳግመኛ

(የፍኖተ ዴሞክራሲ ዜናና ኃተታ) – ነዋሪዎችን ያነጋገረ አንድ የውጭ አገር ጋዘጠኛ ሕዝባዊ አመጽ ዳግመኛ ሊከሰት እንደሚችል ዘገበ – የበቆሎ ምርት ጨራሽ የሆነውን የተምች ትል ለመቆጣጠር አለመቻሉ አሳሳቢ ሆኗል – ኬኒያ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ታሰሩ – አልሸባብ በሶማሊያ ፑንትላንድ ግዛት በአፍርካ…

ኮለኔል አስናቀ እንግዳ: ስራቸውን ጨርሰው ያረፉ ጀግና

ኢያሱ ዓለማየሁ – . . . ለጀግና አያለቅሱም ተብሏል። ጀግኖች ሞትን አይፈሩምና ዘጠኝ ሆኖ ቢመጣም አንድ በአንድ ግባ Colonel Asnake Engidaየሚሉ ናቸው። የጀግና ጀግና፤የወርቅ ዜጋ ምሳሌ የነበሩት ኮለኔል አስናቀ ስለ ታሪካዊ የሕይወት ሂደታቸው በመጽሃፍ አስፍረውታል። እኔ ስለ እሳቸው ማለት የምፈልገው በትግል ሜዳ በጎንደር ካገኘኋቸው ጀምሮ ለእኔ ለግሌ፤ ለድርጅቴ ለኢሕአፓ፤ ለኢትዮጵያና ለትግላችን ምን አንደምታና ሚዛን እንዳላቸው ምስክርነትን ለመስጠት ግዴታ ስላለብኝ ነው። ኮለኔል አስናቀ እኛ ኩታሮች ሳለን፤ ለንቃትም ለተቃውሞ ሰልፍም ገና ሳንበቃ ዛሬ ታሪክን ማጤን ያቃታቸው የሚያመስግኑትን የዘውድ አገዛዝ ተቃውመው፤ በአፍ ብቻ ሳይሆን በተግባር አጼውንም ለመገልበጥ የጣሩና የእስር ስቃይንም የተቀበሉ ናቸው። ወዳጃቸው ኮለኔል እምሩ ወንዴም ተመሳሳይ የሚያኮራ ታሪክ አላቸው። ሁለቱም በአጼው ስርዓት በደል ለደረሰበት ሕዝብ መብትና ብልጽግናን ለማምጣት መስዋዕትነትን የደፈሩ ናቸው። ከእነሱ በኋላ ነቃን አወቅን ብለን የተነሳነው ወጣቶች  አርአያ የሆኑልን ኮለኔል አስናቀና መሰሎቻቸው ናቸው። ኮለኔል አስናቀ የሀገራቸውን ድንበር ለማስከበርም በጦር ሜዳ የዋሉ ቆፍጣና መኮንን መሆናቸውም መጠቀስ ያለበት ነው።  ሙሉውን  ጽሁፍ ያንብቡ . . .

የክቡር ኮሎኔል አስናቀ እንግዳ አጭር የሕይወት ታሪክ

ኮሎኔል  አስናቀ  እንግዳ ከአባታቸው ከአቶ  እንግዳ ገብረ ማርያም እና ከእናታቸው ከወ/ሮ  ውበቴ ገበረ ሥላሴ  በጎንደር ክphoto1ፍለሀገር፣  በደብረታቦር አውራጃ አየር ማርያም ደብር በጥር  7 ቀን 1906 ዓ/ም ተወለዱ።

ኮ/ል  አስናቀ ለውድ አገራቸው የነበራቸውን  ፍቅር፣ ኢትዮጵያዊ ወኔና ቁርጠኝነት ሀ ብለው የጀመሩት ገና በለጋ ዕድሜያቸው ነበር።  ጊዜው  ፋሽስት ጣልያን ኢትዮጵያን በግፍ የወረረበት  ስለነበር ወጣቱ አስናቀ  ወደ ጎንደር በመሄድ የጀግናውን የደጃዝማች አያሌው ብሩን ጦር ተቀላቅለው ለአገራቸውና  ለሕዝባቸው  ነፃነትና  ክብር በተደረገው መራር የአርበኝነት ተጋድሎ  ቀጥታ ተሣታፊ በመሆን  ጠላትን ተዋግተዋል።

አፄ ኃይለሥላሴ  ወደ ሱዳን መግባታቸው  ሲሰማ፣ ትንታጉ አስናቀ ወደዚያው  ተጉዘው ሶባ በተባለው ቦታ  ወታደራዊ ሥልጠና  የተሰጠውና  በሻለቃ (በኋላ  ጄኔራል)  ዌንጌት ይመራው የነበረውንና የጌዴኦን ኃይል በመባል ከታወቀው ልዩ የጦር ክፍል ጋር በመሆን ወደ አገራቸው ተመልሰው በመግባት አርበኞቻችን አገራቸውን ከጠላት  ነፃ ለማውጣት ባደረጓቸው የሞት የሽረት ፍልሚያዎች ተካፋይ ሆነው የኢትዮጵያን ትንሳኤ ካስገኙ አኩሪ የአገር ባላውለታዎች አንዱ መሆን በቅተዋል።   ሙሉውን ታሪክ ያንብቡ

ኢሕአፓ በጀግናው አርበኛ በኮሎኔል አስናቀ ዕንግዳ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በቁጭት ይገልፃል!

ኮሎኔል አስናቀ ዕንግዳ መላ ዕድሜያቸውን ያሳለፉት፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነት፤ ፍትኅ-ርትዕ፤ ዴሞክራሲ ሥርዓትና ለሀገር ልዋላዊነት ሲታገሉ ነው። በዚኽም ምክንያት የአያሌ ዓመታት እስርና መንገላታት፤ ስደትና ጉስቁልና ተፈራርቀውባቸውል። ይኽንንም በፀጋ ተቀብለው፤ በመርኅ ላይ የተመሰረተ ትግል ሲያካሂዱ በመኖራቸው፤ አርአያነተቸው ለዚያ ሰማዕታዊ ትውልድ አንፀባራዊ ኮከብ…

በደቡብ አፍሪካ ዘራፊዎ ች ያፈኗቸው ነጋዴ ተለቀቁ

( ግንቦት 21 ቀን 2009 ዓ.ም.) –  ከሳኡዲ አረቢያ የተመለሱ ስደተኞች ቁጥር ከ30 ሺህ አይበልጥም – ኢትዮጵያና ሌሎች የአፍሪካ አገሮች ለአዛውንቶች የሚሰጡት የጤና አገልግሎት ደካማ መሆኑን አንድ ጥናት አጋለጠ – በደቡብ አፍሪካ በዘራፊዎች ታፍነው የነበሩ አንድ ኢትዮጵያዊ ነጋዴ ተለቀቁ –…

ኢትዮጵያዊ ነኝ !!

አሥራደው (ከፈረንሳይ) አርነት! – የጥቁር ምድር አርማ፤ ልዕልና! – የጥቁር ክብር ማማ፤ የጥቁር ደም – የጥቁር ዘር፤ የጥቁር ብቃይ – ከጥቁር አፈር፤ __ _ ___ ሙሉውን  ግጥም ያንብቡ

ፍኖተ ዲሞክራሲ የራዲዮ ስርጭት መደመጥ ያለበት ሰባት ምክንያቶች

(ዜናነህ በቀለ) –  ፍኖተ ራዲዮ ስርጭቱን የጀመረው በአገር ቤት ኢሕአፓ ይንቀሳቀስ ከነበረበት ነጻ መሬት ሲሆን እኔ ስርጭቱን ካርቱም ሆኜ በጥሞና እከታተል ነበር። አዳማጭ ጠፋ እንጅ ዛሬ በኢትዮጵያችን ላይ የምናየው ክፉ ነገር ሁሉ በወያኔዎች እንደሚፈጸም ትክክለኛ ግምት ያኔ ሰጥቶ ነበር። አሁን…

የትምህርት ጥራት መውደቅ የወያኔ ፖሊሲ መዝቀጥ ነፃብራቅ ነው

(በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር አባላት ኮሚቴ) –  አስተባባሪ የትምህርት ውድቀት የአገርና የሕዝብ ውድቀት ነው። ስለዚህ አገራችንን ከወድቀት ሕዝባችንን ወያኔ አደንቁሮ ለመግዛት ካላው እርኩስ ፍላጎት ማዳን የሚቻለው ምልዓተ ሕዝቡ ተደራጅቶ የተጀመረውን ሕዝባዊ አመፅ በማስፋፋት የወያኔን ዘረኛ ሥርዓት አስወግዶ በምትኩ ፍትሕ ርትዕ…