Oral
የአማርኛ ምሳሌያዊ አባባሎች
Jan 8th
ማስታወሻ
ከዚህ በታች ያሉትን የአማርኛ ምሳሌያዊ አባባሎች ለመነሻነት አቅርበናል። ከደብተራው አንባቢያን ጋር በመተባበር ስብስቡን ይበልጥ አዳጉሰነው ለተመራማሪዎችም ሆነ ለጸሐፍት ጠቃሚ የሚሆን፣ ከሐገራችን የስነ-ቃል ሀብቶች አንዱ የሆነውን የምሳሌያዊ አባባል ቅርሳችንንም መዝግቦ ለማቆየት የሚያገልግል መዝገበ-ባህር ለማድረግ በማሰብ። አንዳንዶቹ ምሳሌያዊ አባባሎች ባላቸው ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ምጣኔ-ሀብታዊ አንድምታ ሰበብ፣ ከዝግጅት ክፍላችን አመለካከት ጋር የማይሄዱ ቢሆኑም ዓላማችን ሁሉምን በቅርስነት ማመሰባሰብ ነውና አላበጠርናቸውም። እርስዎም፣ እባክዎ የሚያውቋቸውን ምሳሌያዊ አባባሎች ከዚህ በታች ባለው የአስተያየት መስጫ ሰሌዳ ላይ ይፃፉልን። ለሚያደርጉልን ትብብር በቅድሚያ እናመሰግናለን።
የደብተራው ድረ-ገጽ አዘጋጆች።
ምሳሌያዊ አባባሎች
-ሀ-
ሀብት ጤዛ ነው።
ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ አይወጣም::
ሁሉ አማረሽን ገበያ አታውጧት።
ሁሉን አገልጋይ፣ የሁሉም እስረኛ ነው።
ሀብታምና ዓሳማ ከሞቱ በሁዋላ ዋጋቸው ብዙ ነው።
ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው።
ሆድ በጎመን ቢደልሉት፣ ጉልበት በአቀበት ይዝላል።
ሀብት ጤዛ ነው።
ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ አይወጣም::
ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም::
ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ አይወጣም::
ሁሉ አማረሽን ገበያ አታውጧት።
ሁሉን አገልጋይ፣ የሁሉም እስረኛ ነው።
ሀብታምና ዓሳማ ከሞቱ በሁዋላ ዋጋቸው ብዙ ነው።
ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው።
ሆድ በጎመን ቢደልሉት፣ ጉልበት በአቀበት ይዝላል።
ሆድ ሲያውቅ ደሮ ማታ።
ሆድ ያባውን፣ ብቅል ያወጣዋል።
ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው::
ሆድ በጎመን ቢደልሉት ጉልበት በአቀበት ይዝላ::
-ለ-
ለሰውሞተአነሰውአለችቀበሮ።
ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ።
ሌባ ለአመሉ ቅቤ ይልሳል።
ሌባ እናት ልጇን አታምንም።
ሌባን ካሳደገ፣ የገደለ ፀደቀ።
ልብ ካላየ፣ ዓይን አያይም።
ለፋሲካ እርድ የተተወው በግ፣ ገና ላይ በታረደው በግ ሳቀ።
ለቀባሪአረዱት።
ለተቀማጭሰማይቅርቡነው።
ሊበልዋትየፈለጉአሞራዝግራ(ጅግራ) ይሏታል።
ላለፈውክረምትቤትአይሰራም።
ላምአለችኝበሰማይወተቷንእማላይ።
ላምእሳትወለደችእንዳትልሰውፈጃት፣እንዳትተወውልጅሆነባት።
ሌባንሌባቢሰርቀውምንይደንቀው።
ሌባሲሰርቅአይጣላምሲካፈልእንጂ።
ልጅእናቷንምጥአስተማረች።
-መ-
መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ።
ሞኝ ካመረረ፣ በግ ከበረረ።
ሞኝን አንድ ጊዜ ስደበው፣ እራሱን ሲሰድብ ይኖራል።
ምነው እናቴ በእንቁላሉ በቀጣሽኝ።
መቀመጥመቆመጥ።
መጀመሪያሙርጤአለችዝንጀሮ።
ሙያ (ሞያ) በልብነው።
ማር ሲበዛ ይመራል።
ማሽላ እያረረ ይስቃል።
ማንይናገር የነበረ፣ ማን ያርዳ የቀበረ።
ምከረው ምከረው እንቢ ካለ መከራ ይምከረው።
ሞኝና ወረቀት የያዙትን አይለቁም።
-ሰ-
ሰርገኛ መጣ፣ በርበሬ ቀንጥሱ።
ሰይጣን ሲያርም፣ ባህታዊ ያስንቃል።
ሳይጣሉት የተጣላ፣ ሲራብ ያበላ አይረሳም።
ሲሾም ያልብላ፣ ሲሻር ይቆጨዋል።
ሴት በዛ፣ ጎመን ጠነዛ።
ሴት የላከው፣ ሞት አይፈራም።
ሲሮጡ የታጠቁትሲሮጡ ይፈታል።
ሳይከካ ተቦካ።
ስለፍቅር በስምአም ይቅር።
ስም ይወጣል ከቤት ይከተላል ጎረቤት።
ስራ ከማጣ ልጄን ላፋታ።
ስራ ያጣ መኖክሴ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል።
ስንተዋወቅ እንተናነቅ።
-ሸ-
-ቀ-
ቂጣም ከሆነ ይወጣል፣ ልጅም ከሆነ ይገፋል።
ቆማጣን ቆማጣ ካላሉት፣ ገብቶ ልፈትፍት ይላል።
ቀስ በቀስ እንቁላል በእግሩ ይሄዳል።
-በ-
በደንባሬ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ።
በጨው ደንደስ በርበሬ ተወደስ።
በቅሎ አባትህ ማን ቢሉት ፈረስ አጎቴ አለ።
ቢከፍቱት ተልባ ቢዘግኑት ጉም።
ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ።
ብርሌ ከነቃ አይሆንም እቃ።
ብልት ቁጠር ቢሉት ጣፊያ አንድ አለ።
በምኒልክ ጊዜ የደነቆረች፣ ምኒልክ ይሙት ስትል ትኖራለች። በሰፈሩት ቁና፣ መሰፈር አይቀርም።
በሬ ካራጁ ይውላል።
ባበላሁ ተነከስኩ።
-ተ-
ታሪኩን የረሳ፣ ካባቱ ገዳይ ይተኛል።
ትለብሰው የላት፣ ትከናነበው አማራት።
-ቸ-
ችኮላ የሰይጣን መልዕክት ነው።
-ነ-
ንብ ሲያረጅ፣ ማር አያመርትም።
ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ።
ኑሮ ካሉት መቃብር ይሞቃል።
-አ-
አመለኛ በቅሎ፣ ማሰሪያዋን ታሳጥራለች።
አመድ በዱቄት ይስቃል።
አንበሳ ሲያረጅ የዝምብ መጫወቻ ይሆናል።
አንገት የተፈጠረው አዙሮ ለማየት ነው።
እንኳን ሲሸጡኝ ሲዋዋሉብኝ አውቃለሁ።
እባብ ያየ በልጥ ደበየ።
እኔ እምበላው ሳጣ ልጄ ጥርስ አወጣ።
እንደምን ዋላቸወሁ ሞፈር እየቆረጥኩ ነው።
አኩራፊ ልጅ፣ ምሳው እራቱ ነው።
አድሮ ጥጃ።
አወቅሽ አወቅሽ ቢሏት፣ የባሏን መጽሐፍ አጠበች።
አውቆ የተኛ ቢጠሩት አይሰማም።
አባይ ማደሪያ የለው፣ ግንድ ይዞ ይዞራል።
አላዋቂ ሳሚ፣ ንፍጥ ይለቀልቃል።
አተርፍ ባይ አጉዳይ።
አያ ጅቦ ሳታመካኝ ብላኝ።
አጥንት የሚቆረጥም ውሻ ወዳጅ አያውቅም።
እውነቱን ተናግሮ ከመሸበት ማደር።
እንዲህ ልጠግብ፣ በሬዬን አረድኩት።
እውነት እና ጅራት ከወደሁዋላ ነው።
እውነት እና ንጋት እያደር ይጠራል።
-ከ-
ከሰው ትህትናን፣ ከአበባ ሽታን ይጠይቋል።
ከድጡ ወደማጡ።
ከዝንጀሮ ቆንጆ ምን ይመራርጡ።
ከሞኝ ደጅአፍ ሞፈር ይቆረጣል።
ከየትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው።
ከአፍከወጣአፋፍ።
ከመምህሩ ደቀ መዝሙሩ።
ከወደቁ ወዲያ መፈራገጥ ለመላላጥ።
ከብት ባልዋለበት ኩበት ለቀማ።
ከልብ ካልቀሱ እንባ አይገድም (አይታገድም)።
-ወ-
ወስፌ ሲለግም፣ ቅቤ አይወጋም።
ወደሽነው ቆማጣ ንጉስ የምትመርቂው።
ውሻ በበላበት ይጮኋል።
-ዘ-
ዘመድ ከዘመዱ አህያ ካመዱ።
ዝም አይነቅዝም።
ዘጠኝ ሞት መጣ ቢሉት፣ አንዱን ግባ አለው።
ዛፎች በጠፉበት፣ ሽንብራም ዛፍ ሆነ።
-የ-
የሚያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል።
የማን ዘር ጎመን ዘር።
የማይጠጡት ጠላ ዓላማውን ስቷል።
የበላበትን ወጪት ሰባሪ።
የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች።
የነገር ወጡ ማዳመጡ።
የተውሶ ጥርስ ቢስቁበት አያደምቅ፣ ቢበሉበት አያደቅ።
የሹም ከርፋፋ፣ አገር ያጠፋ።
የቄስ ነጋዴ ይሆናል ወንበዴ።
የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል።
የዘመድ ጥል፣ የስጋ ትል።
የአንዳንዱ ደግነት ለክፋት አጋጣሚውን በማጣቱ ብቻ ነው።
የአንድ ቀን መዘዝ፣ ያለ ዘጠኝ ወር አይመዘዝ።
ያለበት ይገንበት።
ያደፈን በእንዶድ፣ የጎለደፈን በሞረድ።
የእጅ አመል።
የምጣዱ እያለ፣ የእንቅቡ ተንጣጣ።
የወጋ ቢረሳ፣ የተወጋ አይረሳም።
የፈሰሰ ውሃ አይታፈስም።
የራስዋ እያረረ የሰው ታማስላለች።
የእርጎ ዝምብ።
የተዳፈነ እሳት ነፋስ እሰኪመጣ።
ያለውን የወረወረ ፈሪ አይባልም።
-ደ-
ደፋርና ጪስ፣ መውጫ አያጣም።
ድሃ ሚበላው ቢያጣም የሚከፍለው አያጣም።
-ጀ-
ጅብ የሚያነክሰው ከሜዳ እስከሚደርስ ነው።
ጅራፍ ራስዋ መትታ ራስዋ ተጮኸለች።
-ገ-
(ሲበዛ) ገራምን ልጅ እናቱ አትወደውም።
ጋኖች አለቁና ምንቸቶች ጋን ሆኑ።
ግዛኝ ግዛኝ ብለው፣ ሊሸጠኝ አማረው።
ግም ለግም አብረህ አዝግም።
ተ-
ተማክረህ የፈሳኸው አይሸትም።
ትእግስት መራራ ናት ፍሬዋ ግን ጣፋጭ ናት።
ትሻልን ሰድጄ ትባስን አመጣሁ።
ትለብሰው የላት፣ ትከናነበው አማራት።
ትሻልን ፈትቼ፣ ትብስን አገባሁ።
ትንሽ ቆሎ ይዘህ፣ ካሻሮ ተጠጋ።
-ጠ-
ጠንቋይ ለራሱ አያውቅም።
ጥሩ ማሳ በራሱ ምርት ምርት አያመጣም።
-ጸ-
ጸጉርም የራሱ ጥላ አለው።
-ፈ-
ፈስ ያለበት፣ ዝላይ አይችልም።
እንቆቅልሽ (Riddles)
Jan 8th
ማስታወሻ
እንቆቅልሽ በገጠር እረኞች ወይም አዳጊ ወጣቶች የተፈጥሮ እና የአካባቢ እውቀታቸውን በምስጢራዊ ጥያቄዎች የሚፈታተኑበት ጨዋታ ነው። እንደ ዕውቀት መለኪያም፣ እንደ ጊዜ ማሳለፊያ መዝናኛም።
ጠያቂው ፡ "እንቆቅልሽ/ህ" በማለት ይጀምራል።
ተጋጣሚውም፡ "ምን አውቅልህ" ትለዋለች/ይለዋል።
ጠያቂውም ጥያቄውን ያስከትላል፣ ለምሳሌ "ዞሮ ዞሮ መዝጊያው ጭራሮ" ብሎ። ተጋጣሚው/ዋ መልሱን የሚያውቅ/ታውቅ ከሆነ ይመልሳል/ትመልሳለች። መመልስ ካቃተው/ካቃታት አለዚያም ከተሳሳተ/ተች ግን ጠያቂው "ሀገር ስጠኝ/ስጪኝ" የሚል ጥያቄ ያቀርባል። የሀገሩ/የቦታው ስም ተጠርቶ ለምሳሌ "ዝዋይ" ተብሎ ተሰጠው እንበል፤ እንደሚከተለው የተሰጠውን ሀገር አሞግሶ በመቀበል መልሱን ይናገራል – "ዝዋይ ገብቼ ምን አጥቼ፣ ቢርበኝ በልቼ፣ ቢጠማኝ ጠጥቼ። ዓይን ነው መልሱ" በማለት። ሌላው ተጋጣሚ መልስ እስከሚያውቅ ድረስም በዚህ ሁኔታ ጨዋታው ይቀጥላል። ተጠያቂው/ዋ መልሱን ካወቀ/ቀች ግን የጠያቂነቱን ቦታ ተቀያይረው ጨዋታውን ይቀጥላሉ።
ከዚህ በታች ያሉት የእንቆቅልሽ ጥያቄዎችም የቀረቡት በመነሻነት ነው። ከፊት ለፊታቸውም መልሶቻቸው በማጭድ መሰል መስመሩ () ውስጥ ተቀምጠዋል። የደብተራው አንባቢያን የሚያውቋቸውን ከዚህ በታች ባለው ሰሌዳ ላይ ጽፈው ቢጨምሩበት ደግሞ የስብስባችን ጥራዝ ይበልጥ እንደሚዳጉስ በመተማመን እርስዎንም እጅዎት ከምን እንላለን። የሚያውቋቸውን እንቆቅልሾች እባክዎትን ይፃፉልን። ለትብብረዎ በቅድሚያ እናመሰግናለን።
የደብተራው ድረ-ገጽ አዘጋጆች።
-ሀ-
-ለ-
ላዩ በድን፣ ታቹ በድን፣ መሀሉ ነፍስ አድን። (ድፎ ዳቦ)
እናቷ ጥቁር፣ ልጂቷ ነጭ (ጥቁር ላምና ወተቷ)
-መ-
-ሰ-
ሲቃጠል የሚስቅ ። (ማገዶ)
-ሸ-
-ቀ-
-በ-
-ተ-
ትንሽ መጅ፣ አገር ትፈጅ። (እግር / ጫማ)
-ቸ-
-ነ-
-ኘ-
-አ-
አባቱ ዳኛ፣ ልጁ ቀማኛ። (ጠመንጃ)
እራሱ ገድሎ፣ እራሱ የሚጮህ። (ጠመንጃ)
አይን እያላት የማታይ። (መርፌ)
-ከ-
-ኸ-
-ወ-
-ዘ-
ዞሮ ዞሮ መዝጊያው ጭራሮ። (ዓይን)
-ዠ-
-የ-
-ደ-
-ጀ-
-ገ-
-ጠ-
-ጨ-
-ፐ-
-ጸ
-ፈ-
-ፐ-

