Category: Literature

የገሞራውን አስክሬን ለወያኔ አሳልፎ ለመስጠት ስለሚደረገው ደባ ተጨማሪ ዘገባ

የታላቁን ኢትዮጵያዊ የጥበብ ሰው የኃይሉ ገብረዮሐንስን (የገሞራውን) አስክሬን ለወያኔ አሳልፎ ለመስጠት የሚደረገው ደባ አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል።  ውስጥ አወቅ gemoraw1ምንጫችን እንዳረጋገጠልን፣ የደባው አንቀሳቃሽ ቡድን ስዊድን፣ ስቶክልሆም ውስጥ ሰሞኑን ስብሰባ አድርጎ ለወያኔ ኤምባሲ አቀረበ የተባለው ጥያቄ ከታላቁ የጥበብ ሰው እና የሕዝብ ልጅ ከገሞራው ፎቶ ጋር በአገዛዙ  አምባሳደር በወይንሸት ታደሰ በኩል አዲስ አበባ ላለው የወያኔ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ተልኳል።  የወያኔው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በሀገር ቤት ሰላልነበረም፣ ጉዳዩ በወያኔው ጠቅላይ ሚ/ር ቢሮ ውስጥ፣ በሚ/ር ማዕረግ የዲያስፖራ ጉዳይ አማካሪ ለሆነው ለእንድሪያስ እሸቴ ቀርቦ፣ እሱም በበኩሉ  የወያኔውን ኤምባሲ ጥያቄ ለበረከት ስምዖን መርቶት ነበር።  እጁ በደም የታጠበው ስምዖን በረከትም ከደም አፍሳሽ ጓደኞቼ ጋር ልመካከርበት ብሎ፣ ከነ ስብሃት ነጋ እና ሌሎቹም የወያኔ ቁንጮዎች ጋር ከተመካከረ በኋላ፣ የወያኔ የውጭ ምንዛሬ ላም እና አፍኖ መግዣ የሆነው አየር መንገድ በቅናሽ ዋጋ አስክሬኑን ወደ ኢትዮጵያ እንዲያጓጉዝ ፈቅደዋል ተብሏል።  ሙሉውን ያንብቡ …

ታላቁ ገሞራውን አሳልፈው ለወያኔ ሰጡት !

እሪ በይ ምድሪቷ! እሪ በይ ኢትዮጵያ! ዕድሜ  ልኩን ሶስት ስርዓቶችን ሲዋጋና ሲታገል፤ በዚህም የተነሳ መከራ ሲቀበል የቆየውን ታላቁን ገጣሚና ደራሲ ኃይሉ ገብረ ዮሐንስ  (ገሞራውን) ለርካሽ ጥቅም የተገዙና ለወያኔ የሰገዱ የራሱ ዘመዶች አረፈ በሚል ለጠላቱ ወያኔ አሳልፈው መስጠታቸውን ሀገር ወዳድ ዜጋ…

Link

ደቂቀ ገሞራ፡  ገሞራው በበረከተ መርገም ባነሳቸው ጭብጦች ጠቅለል ተደርገው ሲታዩ የሰው ልጅ በእድገቱ፣ በሥልጣኔው የፈለሰፋቸው ቁሶችና የፈለሰማቸው ይትበሀሎች ለሰው ልጅ ጠቀሜታነት መዋላቸው ቀርቶ ለሰው ልጅ ጥፋትና ውድመት መዋላቸውንና ይህን እኩይ ድርጊት አስፈጻሚና ፈጻሚዎችን ኮነነ፡፡ እረገመ፡፡ ውጉዝ ከመ አርዮስ አላቸው፡፡ እንደ አርዮስ ይለዩ ይረገሙ፡፡ ዝነኛው፣ አንጋፋው ዘፋኝ ዓለማየሁ እሸቴ ያቀነቀነው ፀረ- ኮሎኒያሊዝም የሆነው ያ ጥቁር ግሥላ የተሰኘው ግጥም የደብተራው የጸገየ ወይን ነው፡፡ ስንኞቹ የጸገየ ወይንን የመጠቀ ቅኔ ዘራፊነት ይመሰክራሉ፡፡ በረከተ መርገም ዛሬም ድምጹ በቅኔው ማህሌት በተዘረፈበት ዘመን ሳይቀነበብ የዛሬው ግፈኛ፣ ዘራፊ፣ ዘረኛና ደም አፍሳሽ የሆነው ወያኔንም ከነግፉ ከነግሳግሱ ነፋሪት ያንፍርህ ይለዋል፡፡  ሙሉውን ሐተታ ያንብቡ …

በዝነኛው ኃይሉ ገብረ ዮሐንስ (ገሞራው) ዜና እረፍት የተነሳ

ከኢሕአፓ የተሰጠ መግለጫ:  እውቁ ገጣሚ፥ ታላቁ ደራሲና ግዙፉ የሀገራችን ቅርስ ለረጅም ዓመታት በስደት መከራውን ሲያይ በቆየበት በስቶክሆልም (ስዊድን) ከተማ በዚህ ሰሞን አርፏል። ታዋቂዋንና አቻ የሌላትን በረከተ መርገምንና በርካታ ሊሎች የግጥም መድበሎችንና ድርሰቶችን ያቀረበው ኃይሉ በቤተ ክህነት ትምህርት የላቀ ዕውቀት የነበረው፤…

ሲነድ ሲቃጠል የሚስቅ እሳት ነው! ጋሼ ኃይሉ ገሞራው አልሞተም !

ሀማ ቱማ፡  እውነቱን ለመናገር ታላቁን የኪነት ሰው ጋሼ ብዬው አላውቅም። ኃይሉን ኃይሉ ወይም ገሞራው ነበር ብዬ የምጠራው።የነበረኝ አክብሮት ግን ቅንጣትም ሳይቀንስ። ገሞራው ያኔ በዚያ ጊዜ ለእኛ ወጣቶቹ ዕንቁ አርአያችን ነበር። ተራማጅ የኢትዮጵያ ተማሪዎች አንቀሳቃሶች፤ የመሬት ለአራሹ ሰልፍ አቀነባባሪዎች ተብለው ከዩኒቨርስቲ…

ታላቁ የኢትዮጵያ የጥበብ ዝግባ ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው) (እ. ኤ. አ. 1935 – 2014) አረፈ

የጀርመን ሬዲዮ ጣቢያ የአማርኛ ክፍል ዘገባን ያዳምጡ

gemoraw1

ታላቁ የኢትዮጵያ የጥበብ ዝግባ ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው) ስዊድን ውስጥ በሚኖርበት ሀገር፣ ባደረበት ሕመም ከዚህ ዓለም ተለየ። የሕዝብ ልሳን የሆነውን የጋሼ ኃይሉን ድንገተኛ ማለፍ ስንሰማ፣ የደብተራው ዝግጅት ቦርድ አባላት የተሰማን ድንጋጤና ሃዘን ከፍተኛ ነው። ዝርዝር ጉዳዮችን ወደፊት የምናቀርብ ሲሆን፣ ለመንደርደሪያነት የሚከተለውን አቅርበናል።

ይህ ታላቅ የጥበብ ሰው ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው) እ. ኤ. አ. በ1935 ዓ. ም. አዲስ አበባ ውስጥ ተወለደ። የተወለደበት ባህላዊው ቤት መሠረቱ የተጣለው የዛሬው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ከተሰራበት ቦታ ላይ ነበር። ከህፃንነቱ አንስቶም ቄስ እንዲሆን ይፈልጉ የነበሩት አባቱ መሪ ጌታ ገብረዮሐንስ የቤተክርስቲያን ትምህርት እየሰጡት ነው ያደገው።  ሙሉውን ያንብቡ …