Volume 1
የሞት ጉራማይሌ
Jan 17th
(ከአብርሃም በየነ)
በማዳበሪያ መርዝ፣ ተብክሎ አፈሩ፣
በሞት ጥላ ግርዶሽ፣ ተከልሎ ምድሩ፣
እንደ ቅጠል ሲረግፍ፣ በላዩ ፍጥረቱ፣
የሞት ሳል ይስላል፣ እንደ ሰው መሬቱ።
ተረት ተረት
Jan 7th
(ከሄኖክ ታ. የሺጥላ)
ተረት ልንገርሽ ህይወቴ፣
እንቺ አድምጪኝ በሞቴ፣
ተረት ቢሉሽ ተረት ተረት፣
የዘመነኛችንን ምጥቀት፣
አዲሱን ኢትዮጵያዊነት
እየጠፉ አለሁ ማለት፣
እየጠፉ ያልፋል ማለት፣
ተረት ትረት።
እሽሩሩ – ሩሩ – ኦሶ ሃዬ ሃዬ
Jan 6th
(ከገንባው)
መቼ ንብረታቸውን፣ ባንካቸውን ደፍሮ፣
ጣቱን ቀስሮ እንጂ፣ መቼ እጁን ሰንዝሮ፣
ገዳዩስ ድምፁ ነው፣ ጠንቀኛው ጉሮሮ።
ልጄ አፍህን ዝጋ! አታልቅስ ላይረባ፣
በየአምስት አመቱስ፣ እኔስ ለምን ላንባ፣
ድምጽህ ጠላትህ ነው፣ ጉልበትህን ገንባ።
ለሳሙኤል ዓለማየሁ
Dec 30th
እህታቸው ሀና ዓለማየሁ ያቀረቡትን የሀዘን እንጉርጉሮ ያንብቡ
ሀማ ቱማ

ቆሞ መሄድ ከብዶ፣ ሰብዕናን ጠብቆ፣
መንበርከኩ ሰፍኖ፣ ከጭቃው ውስጥ ገብቶ፣
የሰው ሰውነቱ ትርጉሙ ሲፈለግ፣
ባሻገር፣ ባሻገር
ከአስመሳይነቱ፣
ከአፋዊው ፋኖ፣
ቆንጆ የሁሉም ናት
Dec 21st
አሥራደው (ከፈረንሳይ)
አንደኛው አግኝቶ፣ ውዴ ፍቅሬ ሲላት፣
ሌላው በማጣቱ፣ ጧት ማታ ሲመኛት፣
የውበት ዕድምተኞች፣ እያዩ ሲያደንቋት፣
ያላየው እያየ፣ ውበቷን ሲጎመዥ፣
ምኞቱን ለማስመር፣ ዐይኑ ሲንቀዠቀዥ፣
የሰማው ላልሰማ፣ ዝናዋን ሲረጨው፣
በውበት ረሃብ፣ ምራቁን ሲያስውጠው፣


