የለገጣፎ ሰቆቃ


ግጥም


ጥረገው እንባህን ተው ቻለው ወገኔ፣
ነቃ በል ከእንቅልፍህ ሳትባንን እንደእኔ፣

ስቃይህ ቀጣይ ነው የሌለው ውሳኔ፣

ዘረኝነት ነግሦአል ከፍቶ እንደ ወያኔ::


በመጽሐፍ ቁልቁሉ ቃል ኪዳን ሰጥተውህ፣

በፍቅር ሰበካ ተመርዞ ልብህ፣

ተረድተው መደመር መሆኑን ምኞትህ፣

በኢትዮጽያዊነት ሱስ እያቁለጨለጩህ፣
ላኩልህ ቡልዶዘር ገደል ሊጨምሩህ::

እንደ ሆዳም በሬ ሳር ሳሩን እያየን፣
የቡራዩ ሮሮ ትምህርት ሳይሆነን፣
ለቂሊንጦ ሸገር ስትገብር ልጆቹአን፣
በርካሽ ድለላ አልፈን እንዳልገባን፣
የለገጣፎን ግፍ ልንመስክር በቃን::

ስናቆላምጠው ብለን የጋራችን፣
የዘመኑ ሙሴ የሚል ስም አውጥተን፣
ከሀገር ሱሰኝነት በጥብቁ አቆራኝቶን፣
እንዴት ከመቅጽበት ከዳን መመኪያችን?

አዲስ አበባችን ታስቦ እንድትለማ፣
መስሎን ደፋ-ቀናው እስካምቦ ከተማ፣
ቸኩሎ ለማሞጣት ያን ታከለ ኡማ፣
ተንኮል ኖሮአል ለካስ ያልወጣ አደባባይ፣
ተጋልጧል ጭካኔው በለገጣፎ ላይ፣
ፊቱን ሲያዞር መሪው እያዬ እንደማያይ፣
ህሊናው ሳይወቅሰው በእናቶች ስቃይ::

በወያኔ ሴራ ያልተዘናጉብሽ፣
ከእንግዲህ ባዶ ቃል የማይደልልብሽ፣
ከዘረኛ ትእቢት የሚንከባከቡሽ፣
ታሪክ ከላሾችን እጅ የሚያስነሱልሽ፣
አትደንግጪ ሸገር ነቅተዋል ልጆችሽ::

ተነስ ያገሬ ሰው ቆንጮራውን መክት፣
ተደራጅ ፣ተማከር፣ ተሳሰር በሕብረት፣
ልብህ ሳይሸበር በጠባቦች እብሪት፣
ከደቡብ ጽንፈኛው ከስሜን ህወኃት፣
አድን ወገንህን ከማይቀረው እልቂት::

ከሰላም በየነ