በኦስሎ ፀረ አብይ ስላማዊ ሰልፍ ተደርጓል


በዲሴምበር 10፣ 2019 የአብይ አህመድ የኖቤል ሽልማትን አስመልክቶ በዕለቱ ከቀኑ 12:00 ሰዓት ጀምሮ ኢትዮጵያውያን ስዊድንና ኖርዌይ የሚኖሩ ተቃዋሚዎች በጋራ በመሆን በተቀናጀ መልክ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል፡

ከስዊድን አውቶቡስ ተከራይተው ሌሊቱን ሲጓዙ አድረው ኖርዌይ ከምንገኝ ኢትዮጵያውያን ጋር ተገናኝ ተ ን በተሰጠን ቦታ ላይ ተሰባስበን በኦስሎ ሲቲ ካውንስል ፊት ለፊት አገራችን ኢትዮጵያ የምትገኝበትን አሳሳቢ ሁኔታና አደጋ ሕዝባችንም በታሪክ ታይቶ ተስምቶ በማይታወቅ ከፍተኛ ሰቆቃና የጅምላ ጭፍጨፋ፣ ዘር ለይቶ የማጥቃት፣ መንግስታዊ ሽብርተኝነትና ሥርዓታዊ መድሎ ይህ ተባብሶም በጋሞው፣ በአፋሩ በተለይም በአማራ ህዝብ እየተደረገ ያለው አሰቃቂ ጥቃት፣ በቤተክርስቲያንና በአረመኔያዊ ተግባር የኦርቶዶክሳውያን ጭፍጨፋና በዩንቨርስቲዎች ላይ የሚደርሰውንማሽበርና ግድያ ለዚህም ዋናው ተዋናይ አብይ እንደሆነና ከሌሎች ጽንፍኛ የኦሮሞ አክቲቪስት ነን ባይ ባለሜንጫዎች ጋር ተጠያቂ በመሆኑ ይህንን ድርጊት ለማጋለጥ ለወገኖቻችን ድምፅ ለመሆን ጮክ ብለን ድምፃችንን አሰምተናል።


እኛ ሰልፉን በምናካሂድበት ስዓት በስተቀኝ በኩል ተሰባስበው የመጡ ምን እንደሆኑ የማናውቃቸው ደጋፊዎች ሳያስፈቅዱ በመምጣታቸው ፖሊስ በትኗቸዋል> በኖቤል ሽልማቱ ላይ ውስጥ የገቡ አደግዳጊዎች የወገን ጣር የማይሰማቸው ማፈሪያ አሽቃባጮችና ሆዳሞች እንኳን ጨፈጨፍክልን፣ቤተክርስትያን አስቃጠልክልን፣ ምዕመናንን አስገደልክልን፣ ሕዝብ አፈናቀልክልን፣ ሰው ዘቅዝቀህ አሰቀልክልን፣ አማራውንና ኦሮሞ ያልሆኑትን በሜንጫ አሳረድክልን እልልልል የምያስብል ነበርን? ለዚያውም እንባ እያቀረሩ ማጭብጭብ።


እኛ ለዚህ ሰው ሆነ ለአገዛዙ የሚሰጠው ሽልማት ከሩንዋዳው የባሰ የጅምላ ጭፍጭፋንና የዘር ማጽዳት ተግባርን የሚገፋፋ በመሆኑ ይህ ሰው በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት መቅረብ ያለበት ወንጀለኛ እንጅ ለሽልማት መብቃት እንዳልነበረበት በአስራጨነው ወረቀቶች በበቂ አሰራጭተናል አሳውቀናልም። የያዝናቸው ገላጭ መፈክሮችም፡

Abiy is a killer and criminal!
Abiy´s rule is engaged in terror, brutality and genocide!
Abiy must face charges for genocide!
States and donors must stand for human rights!
አብይ ለሰላም ተሸላሚ ሳይሆን ጸረ ሰላም ነው!
Stop intimidating Eskindir´s movement!
Abiy must be held accountable for death of innocent Ethiopians!
Ethnic federalism is a recipe for disaster through division!
Shame on you Norwegian nobelcommittee! You reward Ethiopian Tyranny!!
የመሳሰሉት ነበሩ