አቅጣጫውና ግቡን ያላወቀ ለውጥ ከንቱ ነው

በፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ራዲዮ – በሀገራችን ለመሰረታዊ ለውጥ ሲካሄድ የነበረው ሕዝባዊ ተደናቅፎ በባእዳን ድጋፍ የይስሙላ ለውጥ ሂደት ከተጀመረ ወራትን አስቆጥሯል። ሕዝብ የሚጠበቀውን ጉጉትና ፍላጎት ለሟሟላት ገና አልተሳካለትም ብሎ መደምደሙ ምክንያታዊ ነው ማለት ግን ይከብዳል። ዘመናትን ያስቆጠሩ ሀገራዊ ችግሮችን በወራት ቀርቶ በዐመታት ለማስወገድ፤ የበርካታ ኃይሎችንና የመላውን ህዝብ ትብብርንና ንቁ ተሳትፎን ይጠይቃል። ሕዝባዊና ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን መገንባት ከወሳኞቹ ጉዳዮች የመጀመሪያውን ረድፍ ይይዛሉ። እነኝህን ሁሉ በግምት ወስጥ ማስገባት ለሚታሰበው ዐላማ ስኬታማነት ዋስትና ይሆናሉ። ከሁሉ በፊት ግን የዴሞክራሲ ግንባታ የቅድሚያ ቅድሚያ ጉዳይ ሊሆን ይገባል። እነኝህን ወሳኝ ጉዳዮች ታሳቢ አድርጎ መንቀሳቀስ አማራጭ አይኖረውም። ሙሉውን ሀተታ