የት ደርሰናል?

ዴሞ (ቅጽ 45፣ ቁ 5፣ ሐምሌ 2012) – . . . በድጋሚ አጽንኦት ሰጥቶ መገንዘብ የሚያስፈልገው ሀገር መገንባት ታላቅ ራዕይ ይዞ ለሚነሳ የሚከብደውን ያህል፣ በአንፃሩ ማጎብደድና ራስ ወዳድነት ስር ከሰደደ በጥቂት ህሊናቢሶች በቀላሉ ሊፈርስ ይችላል። ትናንት የወያኔ መሳሪያዎች የነበሩ ናቸው ዛሬ መሳቂያ በሆነ ተረት ተረት መንጋ አሰማርተው ዜጎቿን እያሳረዱ የባዕዳንን መሠሪ ተልዕኮ እየተወጡ ያሉት። አለመታደል ሆነ አንጂ፣ በዚህ ጊዜ ነበር ወገን በተራበ አንጀቱ ግብር ከፍሎ ያስተማራቸው ምሁራን፣ በለስ ቀንቶት ቤተመንግሥት የገባውን ሁሉ ከማወደስ ይልቅ፣ ሕዝብን እኔ አውቅልሃለሁ ለሚል አምባገነን አሳልፎ ከመስጠት ይልቅ፣ ዴሞክራሲያዊ መብቱ ተከብሮ፤ በዕኩልነት ላይ የተመሠረተ አገራዊና ሕዝባዊ አንድነቱ ተጠብቆ፣ ከማያባራ ሰቆቃ እፎይታ አግኝቶ፣ አገሩንና የራሱን የኑሮ ደረጃ የሚያሳድግበት እድል ባለቤት ለመሆን እንዲበቃ የትግሉ ፋና ወጊ መሆን ይጠበቅባቸው ነበር። የተወሳሰበውን አፍታቶና የተጣመመውን አቃንቶ ሕዝብ የራሱ ዕድል ባለቤት ማድረግ ኃላፊነታቸው ነበር። በአገራችን ዛሬ ላይ የሆነው ግን ፍፁም ተቃራኒ ነው። ሕዝብ ታግሎ ካወረደው ዘረኛ አገዛዝ አብራክ የወጣውን አፈጮሌ እንዲሰየምበት ያለምንም ሀፍረት ተባበሩ። በነዚሁ ክፍሎች የክህደት ጭብጨባ ታጅቦ የትናንቱ የወያኔ ሰላይ ኮሎኔል በብርሃን ፍጥነት ቀለሙን ቀይሮ ቦታው ላይ ተቀመጠ። ይህ የጎጥ ክፍፍልን ለማጦዝ ቀደም ሲል አወሊያን ያቆመ ፀረ ኢትዮጵያ እና ፀረ አማራ የትሮይ ፈረስ፣ ድብቅ ተልዕኮውን ለመወጣት ባገኘው ዕድል ተሳክሮ በዘር ጥላቻ የደነደኑ ኦነጎችን ከነትጥቃቸው ማስገባቱ አንሶት፣ ጎራዴያችን በክርስቲያንና የአማራ ደም ይቀላል ባዩን ባለሜንጫ ከሚዲያ መድረኩ፣ በተቃዋሚ ሽፋን ከሻዕቢያ ጋር ገጥመው አርበኞችን ያሳፈኑና በውጭ ያለውን ማኅበረሰብ በሀሰት ወሬ ገንዘቡን የዘረፉ፣ የአንድነቱን ኃይል ለማዳከም ኦነግን ከመቃብሩ ያውጡ ቅጥረኞችን፣ ከሀዲ አንጃዎችንና አጠቃላይ ፀረ ሕዝብ ግለሰቦችን በክብር ጠርቶ በዙሪያው አሰለፈ::

ወትሮውንስ ሹሙ በፀረ ሕዝብነቱ ሰይጣንን የሚያስንቅ ባይሆን ኑሮ የአድዋዎቹን ቀለበት አልፎ የደህንነቱ ቁልፍ ቦታ ላይ ባላስቀመጠው ነበር። አይነቁም በሚል ይመስላል ሰላሳ ጊዜ የኢትዮጵያን ስም ጠርቶ ዲስኩር ቢያበዛም፣ ላይ ላዩን እያባበልክ ውስጥ ውስጡን አፅዳ ስልት አርጎ እንድሚጠቀም ገና ከጠዋቱ የነቁበት ቢኖሩም፣ በመንጋ የሚነዳውን ቀልብ እስካሁን ስቦለታል። ይኸው ሰሞኑን አጨብጭበው ለቤተመንግስት ያበቁትና ተመክሮ ከስሜት ጉዞ ያላገዳቸው የዕድሜ አዛውንቶች፣ ኮሎኔሉ ሥልጣን ከያዘበት ጀምሮ አስካሁን ሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን በደል አናይም ብለው ድጋፍ ሲያሰባስቡለት እየታዘብን ነው። ለሚያስተውል ዜጋ ስውር ያልሆነው ጉዳይ፣ ኦፒዲኦ በሚል ወያኔ የፈጠረው የኦሮሞ ክንፍ፣ ኦነግ በተወስኑ ዓመታት አማራና ክርስቲያኑን ከኦሮሚያ ለማፅዳት (የዘር አልቂት ማካሄድ ማለት ነው) በዕቅድ ያቆየውን ዓላማ እያስፈፀመ ለመሆኑ በመከላከያ፣ በፀጥታ፣ በአስተዳደር ቁልፍበሆኑ የኢኮኖሚ ተቋማትና ብልፅግና በሚለው ጉረኖ ውስጥ የተሰገሰጉትን የኦሮሞ ፅንፈኞች ማየቱ ብቻ በቂ ነው። ሙሉውን ያንብቡ . . .