የአዲስ አበባን ማንነትና ይዘት በመደገፍ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ኢሕአፓ ይደግፋል

ከኢሕአፓ – እሁድ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ በባልደራስ አዳራሽ ስለ አዲስ አበባ ምን ይደረግ በሚል ውይይት የሚደረግ መሆኑን ተገልጿል። ኢሕአፓ ይህን ስብሰባም ሆነ የአዲስ አበባን ማንነትና ይዘት በመደገፍ የሚደረገውን ማንኛውንም እንቅስቃሴ የሚደግፍ መሆኑን ይገልጻል። በላያችን ላይ በአሜሪካ የተሰየሙብን ሹሞች ዋና ገጽታቸው ዘረኝነትና ጠባብ ወያኔያዊ ግን የኦሮሞ ብሄርተኛነት መሆኑን ስናጋልጥ ቆይተናል። ኢትዮጵያዊነት ሱሳችን ነው ሲሉ የነበሩት ግለሰቦች ዋና መልእክታቸው ተጨፈኑ እናሞኛችሁ እንጂ በልባቸው ኦሮሚያን ለማስቀደም ቆርጠው መነሳታቸውን ከመጀመሪያው ያጋለጥነው ነው። ዛሬ በይፋ አዲስ አበባን ለመጠቅለልና የኦሮሞ ነው በማለት የሚንቀሳቀሱት ክፍሎች ቀጥለውም ከድሬ ዳዋ እስከ ወሎ ደረስ ኦሮሚያ ነው በሚል ቅዠት ሕዝብን ሊያፈናቅሉ፤ ሊፈጁና ሊያስፈጁ ተነትሰዋልና ይህንን በመቃወም የሚወሰዱ ሕዝባዊ እርምጃዎችን ሁሉ ኢሕአፓ ሙሉ በሙሉ መደገፉን መግለጽ ይፈልጋል። ተንጋግተው ወደ አዲስ አበባ የሄዱትና ተቃዋሚ ድርጅት ነን የሚሉት የፖለቲካ ድርጅቶች ሁሉ ጠባብ ብሄርተኞች ኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ሲፈጽሙ እያዩ በለሆሳስም ቢሆን መቃወም አለመቻላቸው ለትዝብት የሚያበቃቸው ከመሆኑ በላይ ተቃዋሚና መሆን አቅቷቸው የጠባቦቹ አወዳሽና ተለጣፊ መሆናቸው አሳዛኝ ድርጊት ሆኖ ይገኛል። ሙሉውን መግለጫ ያንብቡ