የአገራችን ሁኔታ ምን ይመስላል? ምንስ መደረግ አለበት?

የኢሕአፓ ልሳን (ዴሞ. ቅጽ 40፣ ቁ. 2): ወያኔ ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ የነበረው ሁኔታ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ የተገለጸና አሁን በአገር ውስጥ ያለውም ሁኔታ ለብዙ ዜጎች በግልጽ የሚታይ ቢሆንም የአገራችንን ሁለንተናዊ ሁኔታ በየጊዜው እየዳሰሱና እየገመገሙ አጠቃላይ ግንዛቤ መያዝ የወደፊቱን አቅጣጫ ለመቀየስ ይረዳል። ስህተትና ድክመትን አርሞ ጠንካራ ጎንን አፈርጥሞ ትግሉን ወደፊት ለማስኬድና ግቡን እንዲመታ ለማድረግ ያስችላል። በመሆኑም የወቅቱ የዴሞክራሲያ ዕትም የጊዜውን ሁኔታ በመመርመርና የወደፊቱን አቅጣጫ በመጠቆም ላይ ያተኩራል። ሙሉውን ጽሑፍ ያንብቡ…