የኢትዮጵያን ሕዝብ ሰብዓዊ መብቶች መርገጥ ያብቃ!

(ከኢትዮጵያ ፖለቲካ እስረኞች አንድነት ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ) – የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች አሁንም በአስከፊ ሁኔታ እየተጣሱና እየተረገጡ በመሆናቸው ኢፖእኣኮ የተቃውሞ ድምጹን እንደገና በማሰማት መብት ረገጣው ያብቃ ይባላል።

የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ተጠሪ ወደ ኢትዮጵያ መጥታ እየተፈጸመ ያከውን የንብት ጥሰት በቅጡ ሳታነሳ ሴቶች ሚኒስቴሮችና ፕሬዚዳንት መሾማቸውን ቁም ነገር አድርጋ አዳንቃ መመለሷን እንደፈረደብን መታዝብ ተገደናል። ያለውን አገዛዝ ጭፍን ድጋፍ እየሰጡት ያሉት ምዕራባውያን መንግሥታት ሂስና ወገዛ እንዳይቀርብበት እየተከላከሉ መሆናቸው ምንም ክርክርን የሚጠይቅ አይደለም። መብት ጥሰቱ ተጠናክሯል፤ ተስፋፍቷል። ሕዝብ ይፈናቀላል፤ ይገደላልመሬቱንና መብቱን ተነጥቋል። ዘረኝነት መልኩን ቀይሮ ቀጥሏል። ሕዝብን የሚያሰጋው ሌላ ደግሞ ከዚህ በፊት ግድያና ወንጀል የፈጸሙበት ለግፋቸው ሳይጠየቁ የዚህ አገዛዝ አማካሪና ሹም ሆነው መገኘታቸው ነው።

የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ የሚለውን የሕዝብ የቆየ ጥያቄ ጥቂቶችን ለቆ ብዙዎችን በአፈና በማቆየት ሊያልፉት የሚችሉ ይመስል እነሆ ሺዎችን እንዳገቱና የብዙዎችን ደብዛ እንዳጠፉም አሉ። በትንሹ በሚል ወደ ሀምሳ ደብዛቸው የጠፋውን ታጋዮች ስም ብንልካልቸውም እንኳን ሊመልሱ ደረሰንም እንዳላሉ ዛሬ የምናውቀው ነው ።ሕዝብ መብቱን ለማስከበር የሽግግር ሂደትን ሲጠይቅ በጉልበት በላዩ ላይ ተሰይመው ያለፈውን እናስቀጥላለን እንጂ ለውጥ አይኖርም በሚል የዴሞክራሲና የመብት ፍላጎቱን ተቃርነዋል። ስርዓቱን ማስቀጠል ማለት ለ 28 ዓመታት ሕዝብ ያስለቀሰውን አገዛዝ ነፍስ ዘርቶ በሕዝብ ላይ መጫን ማለት መሆኑን ደግሞ በገሃድ እያየነው ነው። በወያኔ ሲገፋ የነበረው ዘረኝነት ዛሬ በአገዛዙ ኦዴፓ ወይም ኦህዴድ አማካኝነት በኦሮሞ የበላይነት ሊተካ ሰፊ ዘመቻ ተጀምሯል። ይህ ደግሞ የተጠበቀውን ጸረ አማራነት ወደ ጽንፍ ወስዶ አማራና አፋሮች፤ ወዘተ በሀይልና በጭካኔ ከቀዬአቸው እየተፈናቀሉና በጅምላም እየተገደሉ ናቸው። በሀገራችን በሞላ ስርዓተ አልበኝነት ሰፍኖና የሕዝብ ስጋት ድርብ ዕጥፍ ጨምሮ እንደሚገኝም ሁሉም ያውቃል። ግብረ ስየልና አረመኒያዊ እርምጃዎች የሀገርን ታሪክ እያጎደፉ ናቸው። አገዛዙ የብሄር ና የሀይማኖት ልዩነትን ማስፈኑ ለሁሉም ግልጽ ሆኖ ይገኛል። መሰረታዊ በሆነ መንገድ የህግ የባልይነትንና ፍትሕን ለማስፈን ይህ ነው የሚባል ጥረትም አልታየም። ዛሬ በፈለጉት ሿሚና ሻሪ ማንም ያልመረጣቸው ባለስልጣኖች ብቻ ናቸው። አጠፉ የተባሉትንም አያያዝ ህግና ስነስርአትን የተከተለ እንዳይደለ ታዝበናል። በመሆኑም ጸረ ሕዝቦች በስፋት እየተሾሙና ሕዝብን ሊያጠቁ ሌላ ዕድል እያገኙ ነው።

እስር ቤቶች ሊዘጉ ቀርቶ በውስጣቸው ተጨማሪ ሰለባዎችን ይዘዋል–የነበረው ግብረ ስየል አልተወገደም። በአንዳንድ ቦታዎች አረመኔዎቹ በስራ ቦታቸው አሁንም አሉ። ሕዝብ ለፍርድ ይቅረቡ ያላቸው ለሹመት ታጩ እንጂ አልተያዙም። አገዛዙ አሁንም መገናኛ ብዙሃንን፤ የህግ አውጪና የፍትህ ከፍሉን ሙሉ በሙሉ ይቆጣጠራል። ጸረ ሕዝብ ጸረ ኢትዮጵያ የተባሉ ህጎችና አዋጆች ቀጥለዋል እንጂ አልተሻሩም። አገዛዙን የለውጥ ሀይል ብሎ ማወደሱ ቢቀጥል፣ የነበረው አገዛዝና ዘረኝነት ዛሬም ቀጥሎ የሕዝብን መሰረታዊ መቶች እየጣሰና እየረገጠ ነው።


ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ !!
የሕዝብ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ያግኙ !!
ሰብዓዊና መሰረታዊ መብቶችን ጥሰት ያክትም !!