የዘር ማጥፋት ዘመቻና የሕዝብ ግድያን እርምጃ ኢሕአፓ በጥብቅ ይቃወማል

ከኢሕአፓ መግለጫ(መጋቢት 30 ቀን 2011 ዓ.ም.) – አካፋን አካፋ የማለቱ ጊዜ መጥቷል። በሰሜን ሸዋ አማራውን ሕዝብ ለመፍጀትና ለማፈናቀል በኦነግ የተከፈተው ዘመቻ የወያኔ ሹሞች እጅም ያለበት ነው። ከአስተናጋጃቸው ከሻዕቢያ ግዛት ወደ አገር ሲገቡ ምንም ትጥቅ ይዘው አልመጡም የተባሉት ዘረኞች ዘመናዊና ያውም ከባድ መሳሪያዎችን ይዘው በማጀቴ፤ አጣዬና ሌሎች ቦታዎች ንጹሁን ሕዝብ ሲፈጁ መታየታቸው፤ መከላከያ ሠራዊት የተባለው ትዕዛዝ አለተሰጠንም በሚል ፍጁ ብሎ ዝም ሲላቸው የጥቃቱ ጠንሻሾች ሹሞቹ ራሳቸው ለመሆናቸው ሌላ ማረጋገጫ የሚያስፈልግ አይደለም። አጼው አያውቁም ሚኒስቴሮቹ እንጂ የሚለው ዛሬ አያዋጣም። ውጭ ሀገር ነበርኩ አላወቅኩም የሚለው የኢሳያስ አፈወርቂ ማወናበጃም ከተጋለጠ ሰላሳ ዓመት አልፎታል። ዛሬ አለምንም ሽፋን መነገር ያለበት ሐቅ ጥቂት የኦሮሞ ጠባቦችና ገንጣዮች–ሹሞችም ጨምሮ–ጸረ ኢትዮጵያና በተለይም ጸረ አማራ፤ ጸረ ጌዴዎ፤ ወዘተ የጽዳትና ጥፋት ፍጅት መጀመራቸው ነው።


በመሆኑም ወያኔ ከጥፋት ዘመቻው ጀርባ መገኘቱ የሚካድ ባይሆንም ለውጥ አመጣን ባይ ሹሞቹ ደግም የሕዝብን ትግል በባዕድ ትእዛዝ አደናቅፈው ዘረኝነትን ማስቀጠላቸው የማይካድ ሐቅ ነው። ከነዚህ ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች ጎን በመቆም ባቀዱት የምርጫ ቧልት ሊደግፏቸው የተዘጋጁትም ያው እንደነሱ በወንጀል ተጠያቂ መሆናቸውን ሁሉም ሊገነዝብና ተገቢውንም እርምጃ ሊወስድ ይገባል። ወያኔና  ሹሞቹ ማለትም ኦነግና ባለሜንጫዎች በአዲስ አበባም በሸዋም ደረጃ አማራውንና ኢትዮጵያ የሚለውን ሁሉ ለማጥፋት በጋራ ተነስተዋል። ቡራዩ፤ ጌዴዎ፤ ለገጣፎ ሱሉልታ፤ ሰሜን ሸዋ፤ ወሎ፤ ወዘተ በግፍና በገፍ እያየን ነው። የዘር ማጥፋት ወንጀል በገሃድ እየተፈጸመ ነው። ጸረ አማራው ዘመቻ በሁሉም ትብብር እየተገፋ ነው። ይህን በግልጽ እያየን ባለንበት ዛሬም ሹሞቹ ኢትዮጵያዊ ናቸው ዘረኞች አይደሉም ብሎ መቃዠት ሀገር አጥፊ ወንጀል እንጂ ሌላም ሊሆን አይችልም። ራስ መጠበቅ፤ መከላከል፤ ሀገር መታደግ ግዴታ እንጂ ቅንጦት አይደለም። ሕዝብ ላይ በትጥቅ ሊፈነጩ የተነሱትን አጸፋውን ብንመልስላቸው ተገቢ ለመሆኑ ማንንም ፍቃድ መጠየቅ የለብንም። የግፉ ምንጭ ግን አሁኑም ሥርዓቱ ነው፤ አሁንም ወያኔና ያሳደጓቸው ቡችላዎች ሹሞች ናቸው። ውሸታቸውን፣ ቅጥፈታቸውን፤ ዘረኛ ድርጊታቸውንም አይተናል፤ ታዝበናል። መደናገርን ለራሳችን ልንፍቅድ አይገባም። ማነህ ተጠያቂና ተሟጋች ለኢትዮጵያ? ማነህ ማነሽ ጎጠኛና ጠባ ብለን መጠየቅና ተገቢውን ምላሽ መረዳት መቻል አለብን። ዛሬ ነገ ተላላ ሆነን አንገታችንን ለእርድ ማቅረብ ሊጠብቅብን አይገባም።


ሊፈጁንና ጸያፍ ጠባብነትን ሊያሰፍኑብን ተነስተው ደማችንን እያፈሰሱ ነው። እምቢኝ ብለን በሁሉም መስክ እንታገላቸው። ሕዝባችንን እንታደግ፤ በጸረ ሕዝቦች አንናወባድ። መፈክራችን ዘረኛው አገዛዝ ይውደም፤ ሕዝብ ሁሉ ተነሳ፤ በተለይ እየተጠቃችሁ ያላችሁት አማራዎችና ሌሎች ሕልውናችሁን በትግል ጠብቁ፤ ኢትዮጵያዊነት ዘረኛዎችን ያውድም መሆን አለበት። ለዚህ ትግል ኢሕአፓ ከጎናችሁ በመቆም ሹሞቹንም አጋሮቻቸውን ሁሉ አምሮሮ አንደሚታገል ቃል መግባት ብቻ ሳይሆን አባላትና ደጋፊዎቹንም ሁሉ ለዚህ ሀገር አድን ታግል በሁሉ መስክ ተሰማሩ ይላል። ጥቃትና ፍጅት እየደረሰባቸው ያሉት ኢትዮጵያውያን ሁሉ በሁሉም መስክ ተደራጅተው ሁለ ገብ ትግሉን በዚህ ዘረኛ አገዛዝ ላይ እንዲያፋፍሙም ጥሪ ያደርጋል።


ዘረኞች ይወድማሉ!
ኢትዮጵያዊነት ያቸንፋል!!
ተደራጁ ታጠቁ ታገሉ !!

Read/Print in pdf