Category: Literature

Link

(አጭር ሥነ ጽሁፋዊ ምልከታ በታምራት ኃይሌ)- ርዕስ፡- የሶሻሊስቱ ጠንቋይ ጉዳይ፣  ደራሲ፡- ሀማ ቱማ፣ ተርጓሚ፡- Hama-amharicሕይወት ታደሰ።  የሶሻሊስቱ ጠንቋይ ጉዳይ The Case of the Socialist Witchdoctor የ 22 አጫጭር ትረካዎች መድብል ሲሆን ትረካዎቹ በሁለት ክፍል ተለይተው ቀርበዋል፡፡ በክፍል አንድ አድራሻቸውን ፍርድ ቤት ያደረጉና በክስ መዝገቦች፤ በክርክሮች፤ በጥፋተኝነት ና በቅጣት ውሳኔዎች ላይ የተመሰረቱ አስራ አንድ ትረካዎች እናገኛለን፡፡ ትረካዎቹ አንድም አስራ አንድም ናቸው፡፡ አንድነታቸውንም አስራ አንድነታቸውንም በኋላ እመለስበታለሁ፡፡ ሙሉውን ያንብቡ …

አሳዛኝ የክህደት ተግባር

ከስዊድን የተላከ ሌላ ደብዳቤ: … ገሞራውን ይበልጥ ሲያሳዝነው የኖረው ግን የባዕዳኑ በደል አልነበረም። ዋነኛው ህመሙ ከሃዲና ከርሳም የኛው አገር ሰዎች ሲፈጽሙበት የኖረው በደል ነው። ገሞራው የሚያምነውን በግልጥ ነግሮ የሚሄድ እንጂ ቂመኛና ተበቃይ አልነበረምና ሊጐዱት፣ ሊያጠቁት ስለተነሱ ሰዎች እንኳን መጥፎ ሲነገር…

Link

ከዘነበ በቀለ: …ነገሩን አወላግደው ለማቅረብ የፈለጉ ግለሰቦች ቪኦኤን ጨምሮ ግጥሙን እንደኑዛዜው በማስመሰል በንባብ ሲያቀርበው ትንሽ እንኳ የማጣራት እርምጃ ልውሰድ አለማለቱ ትዝብት ውስጥ የሚጥለው ነው። … የሚያሳዝነው አሟሟቱ በውል ሳይታወቅ፣ ንብረቱ በህግ ሳይከበር በወንድሞቹ ልጆች አሽቃባጭነትና በአንዳንዶች ቸፍቸፍታ ገሞራው ባልፈቀደው ሁኔታ እንዲቀበር መሆኑ ያሳዝናል። ሆኖም ግን ታሪክና ትውልድ ሲያስታውሱት እንደሚኖሩም ጥርጥር የለውም።  ሙሉውን ያንብቡ…

”ኢትዮጵያዊ ባለቅኔ ሀይሉ ገ/ ዮሐንስ/ ገሞራው’’ በሚል ርዕስ ከአቶ ጥበቡ በለጠ ሰንደቅ የቀረበውን ፅሁፍ በተመለከተ የቀረበ አስተያየት!

ማስታወሻ ከደብተራው ድረ-ገጽ ዝግጅት ክፍል፡  ታላቁ የጥበብ ሰው ገሞራው በ1999 ዓ. ም ’’የቅዱሳንን ዐጽመ-ርስት ርኩሣን አይወስዱትም!  (የማስጠንቀቂያ ጦማር!)’’ በሚል ርዕስ የፃፈውን በሁለት ተከታታይ ክፍሎች ልኮልን በድረ-ገፃችን ላይ አትመነው ነበር።  ’’… የታላቅና ክቡር ውድ አባት ዐጽመ-ርስት የሆነውንና በይዞታው ንብረትነት ለዘመናት የቆየውን…

Link

welelaye-gemoraw

ተንበርክኮ ከመኖር በዓላማ ፀንቶ መሞት ይሻላል!!

በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ ዝነኛው ገጣሚና መምህር ኃይሉ ገብረዮሐንስ በስደት ከሚኖርበት አገር ስዊድን( ስቶኮልም ከተማ) ጥቅምት መጨረሻ 2007 ዓ.ም ማረፉን የሰማው በከፍተኛ ሀዘን ነው። ሃይሉ ገብረዮሐንስ በመምህርነት ሙያው እንደ አንድ ሃላፊነት የሚሰማው ዜጋ ሀገር ወዳድ ትውልድ ለመፍጠር…

የታላቁ ኢትዮጵያዊ የስነፅሑፍና የፍልስፍና ሰው የኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው) ዕለተ ትንሣዔ

ከስቶክሆልም የተላከ: ለዚህ ፅሑፍ ዕለተ ትንሣኤ! የሚል ርዕስ መስጠት የፈለግሁት ካለምክንያት አይደለም። አንድ ቀን ኃይሉን ለመጠየቅ ቤቱ ሄጄ፣ ‘’እንደምን ሰንብተሃል? ጤንነትህስ እንዴት ነው?’’ ስለው ከሰጠኝ መልስ በመነሳት ነው።  “ደህና ነኝ! ሰው እኮ በህይወት እስካለ የሚቻለውን መልካም የሆነን ነገር ሁሉ እያረገ…

Link

ከዘነበ በቀለ:  ከሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ያላችሁ የኔንና የገሞራውን ቅርበት የምታውቁ ወገኖቼ  ላደረጋችሁልኝ ማፅናኛ ከልብ እያመሰገንኩ ገሞራውን በተመለከተ ላቀረባችሁት ጥያቄ መልስ መስጠት በማልችልበት ሁኔታ ላይ ስለነበርኩ መልስ ለመስጠት አልቻልኩም ነበር። አሁን ግን የሀይሉ ገሞራውን  አስከሬን በተመለከተ የሰሞኑ አስገራሚ ትዕይንት ተጠናቆ አስከሬኑን ወደ ኢትዮጵያ የላኩት በመሆኑ ይህንን መለስተኛ ማስገንዘቢያ ለመፃፍ ተገድጃለሁ። ምንም ሳልናገር በመቆየቴ ይቅርታ እየጠየቅሁ ሁኔታው ከዚህ በሚከተለው መልኩ የተጠናቀቀ መሆኑን በትህትና እገልፃለሁ። ሙሉውን ደብዳቤ ያንብቡ …