”ኢትዮጵያዊ ባለቅኔ ሀይሉ ገ/ ዮሐንስ/ ገሞራው’’ በሚል ርዕስ ከአቶ ጥበቡ በለጠ ሰንደቅ የቀረበውን ፅሁፍ በተመለከተ የቀረበ አስተያየት!

ማስታወሻ ከደብተራው ድረ-ገጽ ዝግጅት ክፍል፡  ታላቁ የጥበብ ሰው ገሞራው በ1999 ዓ. ም ’’የቅዱሳንን ዐጽመ-ርስት ርኩሣን አይወስዱትም!  (የማስጠንቀቂያ ጦማር!)’’ በሚል ርዕስ የፃፈውን በሁለት ተከታታይ ክፍሎች ልኮልን በድረ-ገፃችን ላይ አትመነው ነበር።  ’’… የታላቅና ክቡር ውድ አባት ዐጽመ-ርስት የሆነውንና በይዞታው ንብረትነት ለዘመናት የቆየውን ቦታ ኢሕጋዊ በሆነ መንገድ በዘረፋ ወስደዋል። … ’’ በማለት ጀምሮ ’’… አሁን ይህን ቦታ በዳረጎትነት ተሰጠኝ ብሎ የሚጨፍረውና ጮቤ የሚረግጠው ሰው በቀጣዩ የፍትሕ ወቅት የደም እንባ ከሚያለቅስ ዛሬውኑ አስረክቦ ዞር ቢል ይመረጣል።  … ’’  ብሎ ያጠቃለለውን ጽሑፍ የደመደመበትን ግጥም (ቀጥሎ በቀይ ቀለም የተቀመጠው) ያልሆነ ትርጉም እየሰጡ፣ ጥቂት ሰዎች የዚህን ክቡር የኢትዮጵያ ልጅ አስክሬን ከወያኔ ጋር ለመሞዳሞድ ሲያውሉት ታዝበናል።  ይህን ጉዳይ በተመለከተ በ እኛ በኩል በሰፊው እንመለሥበታለን።  ለዛሬው የቅርብ ወዳጃቸው አቶ ዘነበ በቀለ የላኩልንን  ጽሑፍ ከዚህ በታች አቅርበናል።  ጽሑፉን ያንብቡ …