ፋኖ-የነፃነት አርበኛ

በመኩሪያ አድማሱ ስታክተን, ካሊፎርኒያ 17 May 2024

ምን ያለው ብር ነው? ወድቋል ተሽቀንጥሮ፣

ዲስኩርህ ሰለቸን— ውሸት ተከምሮ፣

በነፃ አስቦ በነፃ ተናግሮ፣

ሕዝባችን ይኖራል በፋኖ ተከብሮ::

 በተንኮል በዕብሪት— አንገት ማስደፋቱ፣

 ሽብርን ሲያሰፍን— እንዲፈስ ሃሞቱ፣

ቁረጥ አንደ ፋኖ— ያ ነው መድሃኒቱ::

 አምባገነን ያያል–- አንተን እያስራበ፣

 ያፈናቅልሃል— ላንተ መች አሰበ::

ገዳይ ካሕናትን— ከመቅደሱ ግቢ፣

የቆሎ ተማሪን— በድሮን ደብዳቢ፣

 እንስሳት ሳይቀሩ— በእሳት አንገብጋቢ::

 ገዳይ ሕፃናትን ገዳይ እናቶችን፣

ዐይናችን ጉድ አየ ተኝቶ ሕዝባችን፣

 ትጥቅ ፍቱ ሲለን ነቃን ከእንቅልፋችን::

 እያሠረ ገዳይ— እየሸሸ አስገዳይ፣

 ፋኖ ይፈታዋል የዚህንስ ጉዳይ::

 ነፃነት ዋጋ አለው— እንዳይኖር ተዋርዶ፣

ያስከፍላል እንጂ— አይደለም በባዶ::

የት ላይ ተወለደ? የትኛው አውራጃ?

እየሞተ ገዳይ— በአዲሱ ጠበንጃ::

 ፋኖ የጀግና ዘር— አዋጂን ሲያወጣ፣

 ትነስና ትመም— ግባ በቆረጣ፣

ጠላትን ይጭነቀው— እኛ የለን ጣጣ ::

የሚሰማ የለም የጠላትን ምልጃ፣

ማን ሞክረን አለው? የዞረውን እንጃ፣

 የፋኖን ገድል ፃፉ— ለታሪክ ማስረጃ::

 በስናይፐር አልሞ፣ መትረየስ ደግኖ፣

በግንባር ተጋፍጦ ጠላቱን በትኖ፣

ደም ልሰጥ ነው አለ— ያ ጀግና! ያ ፋኖ!

ግፈኛውን ሲጥል በፈሰሰው ደሙ፣

ዓለም ይገረማል አስከ ዘላለሙ፣

 ያኔ ነው አልኳችሁ የሚሳካው ሕልሙ::

ጎጃም ላይ ገዳይ– ሞርታር ማራኪ፣

ጎንደር ላይ ገዳይ– ድሽቃ ነጣቂ፣

ወሎ ላይ ገዳይ– ቆርጦ በትኖ፣

ሸዋ ላይ ገዳይ– ጠላት አፍኖ፣

በሞቴ ገዳይ!— ና ፋኖ! ና ፋኖ!