ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባ በኦስሎ ኖርዌይ። የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ የኖርዌይ ክፍል ሕዝባዊ ስብሰባ አዘጋጅቷል። የዕለቱ ተጋባዠ እንግዳ የኢሕአፓ ከፍተኛ አመራር አባል አቶ እያሱ ዓለማየሁ በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ ላይ ይሰጣሉ። ጸሀፊ እና የምሥራቅ አፍሪካ ኤክስፐርት የሆኑት አቶ ዮሱፍ ያሲን የማንነት ፖለቲካ፣ ብሄርተኝነትና የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ በሚል ርዕስ ያወያዩናል። ወጣቱ ምሁር ዶክተር ተክሉ አባተም የአማራው ፖለቲካዊ ንቅናቄና አንድምታው በሚለው ርዕስ ላይ ያወያየናል። በተጨማሪም ከኖርዌይ የድርጅቱ የወጣቶች ክፍል ጥሪ ይተላለፋል። በአካባቢው የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ በሰዓቱ ተገኝታችሁ የውይይቱ ተሳታፊ እንዲትሆኑ በአክብሮት ተጋብዛችኋል።
በዕለቱ ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሬዲዮን ለመርዳት ምሳና ለስላሳ ለሽያጭ ይቀርባሉ።
የስብሰባው ዕለት: 18 Feburary 2017 ሰዓት፡ 15:00 – 18:00
የስብሰባው ቦታ: Antirasistik senter, Storgate 25, 0103 Oslo, Sentrum