“ሀገርንና ሕዝብን ባለመክዳታችን ፤ አብሮን የሚኖረው ኅሊናችን ሲያመስግነን ይኖራል!”

ከፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሀተታ – የኢሕአፓ ታጋዮች፤ እንደ አብረሐም ቤት የሌላቸው፤ እንደ ሙሴ መቃብራቸው ያልታወቀላቸው፤ የቤተስብ ባይታዎሮች፤ የዓለም ተንከራታቾች መሆናቸውን ያውቃሉ። በዚህ አይቆጩም። ነገር ግን፤ ፓርቲያቸው የወቀሳ ዶፍ እንጅ፤ የምስጋና ካፊያ ያልተቸረው በመሆኑ ቅር ይሰኛሉ። ይከፋሉ። ያም ሆኖ፤ የተመስጋኝ ሳይሆን፤ ያመስጋኝ ዕጥረት ያለባት ሀገር መሆኗን ስለምንረዳ አመስጋኝን አንጠብቅም። ሀገራችንንና ሕዝባችንን ባለመክዳታችን፤ ባለመጎዳታችን ፤ አብሮን የሚኖረው ሕሊናችን እያመስግነን ስለሚኖር ግን ደስተኞች ነን። ሙሉውን ሀተታ ያንብቡ