የራሱን ታሪክ የላከበረ ትውልድ፤ በራሱ ላይ ይሞት በቃ እንደፈረደ ይቆጠራል!


ከፍኖተ ዴሞክራሲ፡ የኢትዮጵያ አንድነት ድምፅ ሬዲዮ ወቅታዊ ሐተታ፡
ከኢጣሊያ ፋሽስት ወረራ ማግስት የመጣው ትውልድ፤ አስተዳደጉ፤ በመልካም ሥነ ምግባርና አኩሪ ታሪክ ላይ በተመሠረተ ትምህርት ነበር። በዚህ ምክንያት ከአሁኑ ትውልድ የተለየ መስተጋብርና የታሪክ ግንዛቤ ነበረው። የሀገሩን ታሪክ፤ ባኅል፤ ሃይማኖት፤ የነጻነት ዋጋና ክብር፤ የዐርበኞችን መሥዋዕታዊ ትግልና ጀግንነት በሚገባ ተነግሮታል። በዚህም የተነሳ፤ የሀገር ቃል-ኪዳን አክባሪነትና የወገን ፍቅር ነበረው። ለኢትዮጵያ ሀገሩ ታላቅ ቅርስ፤ ደጀንና ተስፋ ነበር። የቀሰመውን ትምህርት እንደ መልካም አርአያ ስለሚመለከተው የሚጠበቅበትን ብሄራዊ ኃላፊነት ለመሸከም የተዘጋጀ ትውልድ እንደነበር ታሪክ ይመሰክርለታል። ያ ትውልድ፤ በራሱ ዘመን ሦስት ሥርዐት ሲፈረራርቁ ለማየት ቢችልም፤ በመሠረታዊ መልኩ ኢትጵያዊነቱን ጠብቆና አክብሮ የሚኖር ትውልድ መሆኑን በከፈለው መሥዋዕት አስመስክሯል። በመርኅ ላይ የተመሰረተ ጽናቱን ጠብቆ ቆይቷል። ሙሉውን ጽሑፍ ያንብቡ …

በወያኔ ጎራ ጩኸት በረከተ 
ከፍኖተ ዴሞክራሲ፡ የኢትዮጵያ አንድነት ድምፅ ሬዲዮ ወቅታዊ ሐተታ

እንጻፍ ከተባለ

ኢያሱ ዓለማየሁ፡  "የማይጽፍ ደብተራ፤ ክንፍ የሌለው አሞራ።"   ለደብተራነቱ ባልበቃም ደብተራዎችን የማወቅ ዕድል ስለነበረኝና የደብተራውን ደብተራ ጸጋዬ ገብረመድህንን ጓድ የማለቱን ዕድል አግኝቼም ስለነበር አልፎ አልፎ — ብዙውን ጊዜ "አልበዝቶም ለማለት"–ያው አጅሪዎችን የሚያንጨረጭር ጽሁፍ መጻፌ አልቀረም።  ይህም በዚያው መንፈስ ይታይልኝ።  ቁራ መቸም ባይነጣም፤ ማለትም የሚመለከታቸው መቸም የሚታረሙ ባይሆኑም ድምጽ ማሰማቱ ደግሞ ግዴታ ነው።  በተለይ ውድ ሕይወታቸውን ለሀገር በሰጡት ላይ ጸያፍ ዘለፋና ዘመቻ ሲካሂድ።   ሙሉውን ጽሑፍ ያንብቡ

ሶሴፕ አሜሪካ ወኪሉን ወደ ዊኒ ፔግ ይልካል


የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች አንድነት ኮሚቴ (ሶሴፕ) የአሜሪካ ቅርንጫፍ፡  በካናዳ ዊኒፔግ የሰብዓዊ መብት ቤተመዘክር (ሙዚዬም) እ. ኤ. አ. ከ2008 ጀምሮ ሲታነጽ ቆይቶ የፊታችን ሴፕቴምበር 20 በከፍተኛ ድምቀት ለሕዝብ ዕይታ ክፍት ይሆናል፡፡ የካናዳ ሰብዓዊ መብት ቤተመዘክር ዋናው ዓላማው 1ኛ. ስለ ሰብዓዊ መብት ዕውቀትና ግንዛቤ ለማስጨበጥ፣ 2ኛ. ለሌላውም ወገን ከበሬታ ለማጎናጸፍና፣ 3ኛ. ውይይትን፣ ግንዛቤንና ተግባራዊነትን ለማበረታታ ነው፡፡ በዚህ ቤተመዘክር ውስጥ በዓለም ዙሪያ ስለሰብዓዊ መብት የተደረጉትን ታሪካዊ እንቅስቃሴዎችን ከሴፕቴምበር 20፣ 2014 ጀምሮ በቋሚነት ለሕዝብ ክፍት ያደርጋል፡፡ ሙሉውን ጽሑፍ ያንብቡ

The Divide

By Gemencho:    Even at face value the democratic ideals that the domesticated Ethiopian elite claim to uphold are fake.  Democratic ideals are not neutral ideas.  They do not confuse killers with their victims. They do not blur the distinctions.  They take sides.  What is also at issue is a question of identity- a glaring cultural rupture between this elite and Ethiopia.  The two don’t speak the same language. They don’t share the same space. Their goals are diametrically opposite.  Read More…

አቶ ኢያሱ ዓለማየሁ፣ የኢሕአፓ ከፍተኛ አመራር አባል፣ ከፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምፅ ሬዲዮ ጋር ያደረጉትን አዲስ ቃለ-መጠይቅ ያዳምጡ

የመጽሐፍ ትችት፣ “እኛና አብዮቱ” (ክፍል 1) – ከጥበበ ሣሙኤል ፈረንጅ

   የትንሳኤው ጥሪ ለመሆኑ ለማን ነው?  (አቶ ሰውየው ከሰሜን አሜሪካ)

የሱዳኖችና የወያኔ ወታደራዊ ስምምነት (ሊያነቡት የሚገባ ወቅታዊ ሐተታ)

ጽንፈኝነትን ተከላክለን አንድነታችንን እንገንባ (ዴሞ ቅጽ 39፣ ቁጥር 7)

ዴሞክራሲያ፡ የኢሕአፓ ልሳን

ኢትዮጵያ (ሐምሌ/ነሐሴ 2006 ዓ. ም. እትም)
በኢሕአፓ የዲሲና አካባቢው ደጋፊ አካል የሚዘጋጅ ወርሃዊ ጋዜጣ

  • Support SOCEPP

  • Finote-Democracy (14 Sep 2014)

  • EPRP’s 42nd Anniversary (New Video – Part 1 & 2)

  • kedada chereka

    (Click below to read the whole book in Amharic)
  • Why the lies!? how long to the lies!?

  • To Kill A Generation

    THE RED TERROR IN ETHIOPIA (Click below to read the whole book)