ከወክንድ የተሰጠ መግለጫ: ፀረ- ወያኔው ትግል ይፋፋም!

እኛ ወያኔ ከነግሳንግሱ ወደ ታሪክ ትቢያ እንዲወርድ ከመታገል ሌላ አማራጭ የለም ብለን በፅኑ የምናምንና በቀቢፀ ተሰፋ የተሞላን ሰላልሆን፣ ከወያኔ ነጻና ፍትሀዊ ምርጫን አንጠብቅም።  ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል እንዲሉ ወያኔና ሐቅ ሁሌም ለየቅል መሆናቸውን ጠንቅቀን እናውቃልንና። ዴሞከሪሲ ስንል የህዝብ ልዕልና፣ ነጻ…

ህዳር 22 አለም አቀፍ የኤድስ ቀን

ኢሕአፓ፡ ከ1988 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች፡ መግለጫዎችና ትዕይንቶች እየታጀበ በመላው አለም በያመቱ ህዳር 22 የሚታሰበው አለም አቀፍ የኤድስ ቀን ዘንድሮም ካለፈው በበለጠ ሁኔታ እንቅስቃሴ እየተደረገበት ይገኛል። መንግሥታዊ ተቋሞችና መንግሥታዊ ያልሆኑ ሕዝባዊ ድርጅቶች በበሽታው የተጠቁ ዜጎች የሚደርስባቸውን አድሎና የመገለል ሁኔታ ለመግታት…

የሾላ ዛፍ ማፍራት የጠቀመው ለአዕዋፍ ነው፣ ዛፉ አልተጠቀመም!

የፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሬዲዮ ሐተታ፡ በኢትዮጵያ ሕዝብ የረዥም ዘመናት ታሪክ ሂደት፤ ገናና የታሪክ ምዕራፍ አስመዝግቦ አልፏል የተባለለት፤ የየካቲት ወር 1966 ዓመት ምህረት ዐብዮት ነበር።  የኢትዮጵያ ሕዝብ ዐብዮት!  ኢትዮጵያዊ ዐብዮት ነበረ!  ያልተዳቀለ፤ ያልተበረዘ፤ ያልተዘነቀ፤ ያልተበወዘ፤ ያልተለወሰ ያልተደረተ፤ ወጥ (ኦርጂናል)…

ተንበርክኮ ከመኖር በዓላማ ፀንቶ መሞት ይሻላል!!

በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ ዝነኛው ገጣሚና መምህር ኃይሉ ገብረዮሐንስ በስደት ከሚኖርበት አገር ስዊድን( ስቶኮልም ከተማ) ጥቅምት መጨረሻ 2007 ዓ.ም ማረፉን የሰማው በከፍተኛ ሀዘን ነው። ሃይሉ ገብረዮሐንስ በመምህርነት ሙያው እንደ አንድ ሃላፊነት የሚሰማው ዜጋ ሀገር ወዳድ ትውልድ ለመፍጠር…

Link

welelaye-gemoraw

የገሞራውን አስክሬን ለወያኔ አሳልፎ ለመስጠት ስለሚደረገው ደባ ተጨማሪ ዘገባ

የታላቁን ኢትዮጵያዊ የጥበብ ሰው የኃይሉ ገብረዮሐንስን (የገሞራውን) አስክሬን ለወያኔ አሳልፎ ለመስጠት የሚደረገው ደባ አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል።  ውስጥ አወቅ gemoraw1ምንጫችን እንዳረጋገጠልን፣ የደባው አንቀሳቃሽ ቡድን ስዊድን፣ ስቶክልሆም ውስጥ ሰሞኑን ስብሰባ አድርጎ ለወያኔ ኤምባሲ አቀረበ የተባለው ጥያቄ ከታላቁ የጥበብ ሰው እና የሕዝብ ልጅ ከገሞራው ፎቶ ጋር በአገዛዙ  አምባሳደር በወይንሸት ታደሰ በኩል አዲስ አበባ ላለው የወያኔ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ተልኳል።  የወያኔው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በሀገር ቤት ሰላልነበረም፣ ጉዳዩ በወያኔው ጠቅላይ ሚ/ር ቢሮ ውስጥ፣ በሚ/ር ማዕረግ የዲያስፖራ ጉዳይ አማካሪ ለሆነው ለእንድሪያስ እሸቴ ቀርቦ፣ እሱም በበኩሉ  የወያኔውን ኤምባሲ ጥያቄ ለበረከት ስምዖን መርቶት ነበር።  እጁ በደም የታጠበው ስምዖን በረከትም ከደም አፍሳሽ ጓደኞቼ ጋር ልመካከርበት ብሎ፣ ከነ ስብሃት ነጋ እና ሌሎቹም የወያኔ ቁንጮዎች ጋር ከተመካከረ በኋላ፣ የወያኔ የውጭ ምንዛሬ ላም እና አፍኖ መግዣ የሆነው አየር መንገድ በቅናሽ ዋጋ አስክሬኑን ወደ ኢትዮጵያ እንዲያጓጉዝ ፈቅደዋል ተብሏል።  ሙሉውን ያንብቡ …

Link

ደቂቀ ገሞራ፡  ገሞራው በበረከተ መርገም ባነሳቸው ጭብጦች ጠቅለል ተደርገው ሲታዩ የሰው ልጅ በእድገቱ፣ በሥልጣኔው የፈለሰፋቸው ቁሶችና የፈለሰማቸው ይትበሀሎች ለሰው ልጅ ጠቀሜታነት መዋላቸው ቀርቶ ለሰው ልጅ ጥፋትና ውድመት መዋላቸውንና ይህን እኩይ ድርጊት አስፈጻሚና ፈጻሚዎችን ኮነነ፡፡ እረገመ፡፡ ውጉዝ ከመ አርዮስ አላቸው፡፡ እንደ አርዮስ ይለዩ ይረገሙ፡፡ ዝነኛው፣ አንጋፋው ዘፋኝ ዓለማየሁ እሸቴ ያቀነቀነው ፀረ- ኮሎኒያሊዝም የሆነው ያ ጥቁር ግሥላ የተሰኘው ግጥም የደብተራው የጸገየ ወይን ነው፡፡ ስንኞቹ የጸገየ ወይንን የመጠቀ ቅኔ ዘራፊነት ይመሰክራሉ፡፡ በረከተ መርገም ዛሬም ድምጹ በቅኔው ማህሌት በተዘረፈበት ዘመን ሳይቀነበብ የዛሬው ግፈኛ፣ ዘራፊ፣ ዘረኛና ደም አፍሳሽ የሆነው ወያኔንም ከነግፉ ከነግሳግሱ ነፋሪት ያንፍርህ ይለዋል፡፡  ሙሉውን ሐተታ ያንብቡ …