ሃገር አድኑን ትግል እናግዝ እንቀላቀል

ፍጹም መንገሻ (ከኖርዌይ:  ሃገራችን ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሃገራት ከቅኝ አገዛዝ ነጻ መውጣት ለጥቁር ህዝብ ነጻነት ያበረከተችው አስተዋጽኦ ቀላል የሚባል እንዳልሆነ የሚታወቅ ነው።ከዚህም በተጨማሪ ለሙስሊሙ እምነት ባለውለታነቷን ታሪክ የሚፍቀው አይሆንም።ይህ መልካም ተግባሯ በሌላ በኩል ሃገራችንን በአይነቁራኛ እንዲመለከቷት እና አሁን በአይናችን እንደምናየው ባንዳዎችን ቀጥረው እስኪበቀሏት ዳርጓታል።የዛሬው ታሪክን ማጥፋት ሩጫም የነዚሁ ውጤት ሳይሆን አልቀረም። አሁን በሃይል ቦታውን የተቆጣጠረው አገዛዝም ህዝብን በማሰቃየት እና ወደተለያየ ሃገራት በማሰደድ እየተራዳ ለዚሁ የብቀላ ድርጊት ተዋናይነቱን እያሳየ ይገኛል።በየሃገራቱም ያሉ መንግስታት ይህ ህዝብ ተወካይ እና ተጠሪ ያጣ እንደሆነ በመረዳት እስኪመስል እንደፈለጉ እያሰቃዩት ይገኛሉ።  ሙሉውን  ያንብቡ