ህዳር 22 አለም አቀፍ የኤድስ ቀን

ኢሕአፓ፡ ከ1988 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች፡ መግለጫዎችና ትዕይንቶች እየታጀበ በመላው አለም በያመቱ ህዳር 22 የሚታሰበው አለም አቀፍ የኤድስ ቀን ዘንድሮም ካለፈው በበለጠ ሁኔታ እንቅስቃሴ እየተደረገበት ይገኛል። መንግሥታዊ ተቋሞችና መንግሥታዊ ያልሆኑ ሕዝባዊ ድርጅቶች በበሽታው የተጠቁ ዜጎች የሚደርስባቸውን አድሎና የመገለል ሁኔታ ለመግታት እንዲቻል ሁሉም ዜጋ ድምጹን እንዲያሰማና አንድነቱንም በተግባር እንዲገልጥ አፅንዖት የተሞላበት ጥሪ በማቅረብ እየዘከሩት እንደሚገኙ በተለያዩ የዜና ተቋማትና ድረገፆች የሚወጡት ዘገባዎች፡ ትንተናዎችና ትምህርታዊ ገለፃዎች የሚያመላክቱት ናቸው። ሙሉውን መግለጫ ያንብቡ…