ለነፃነት መሰዋት አኩሪ ታሪክን ለአገርና ለሕዝብ ማስተላለፍ ነው!! ትግሉ ሳያቋርጥ ተፋፍሞ ይቀጥል

(በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አስተባባሪ ኮሚቴ) – የወያኔ አጋዚ ጦር በምስራቅ ሐረርጌ በጨለንቆ ሕዝባችን ላይ የወሰደውን ግድያ በማውገዝ ገዳዩ የአጋዚ ጦር አዛዦች ለፍርድ እንዲቀርቡ፣ በተለያዩ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በሚማሩ ተማሪዎች ላይ የአጋዚ ጦር የፈጸመውን ግድያ፣ ድብደባ፣ እስራትና የትምህርት ሂደት ማደናቀፍን በጥብቅ ያወግዛል። በየዩኒቨርሲቲዎቹ በፀጥታ ማስከበር በሚል ሰበብ የወያኔ ነፍሰ ገዳይ አጋዚ ጦር መስፈርን ይቃወማል።  በአስቸኳይ የሰፈረው የአጋዚ ጦር እንዲወጣ በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አስተባባሪ ኮሚቴ አጥብቆ ይጠይቃል። የአንደኛ፣ የመለስተኛና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች መምህራንና ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጎን እንዲቆሙና በትግሉም እንዲሳተፉ ማህበሩ ያሳስባል። እንድነት ኃይል ነው፤ ተባበሩ።  ሙሉውን  መግለጫ ያንብቡ . . .