ልፅደቅ ብየ ባዝላት ትንጠልጥላ ቀረች!

(በፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ራዲዮ የተላለፈ ሐተታ) – ያም ሆኖ ግን፤ እዚህ ላይ፤ የሦስት ከተሞች ተጋድሎን፤ በታሪክ ሳይጠቀስ ማለፍ አይቻልም። እነርሱም ዳባት፤ ደብረታቦርና አምቦ ከተሞች ነበሩ። ወራሪውን የወያኔ ጦር በጀግንነት ተጋትረው እረፍርፈዉታል። የወያኔ ጦር የደብረታቦር ከተማን፤ በቀላሉ አልያዛትም። ሕዝቡ 72 ሰዓት ተዋግቷቸዋል። ወያኔ አዲስ አበባ ሊገባ የቻለውም፤ በእነኝህ ከተሞች ጀግኖችና በኢሕአፓ ቆራጥ ታጋዮች ሬሳ ተረማምዶ ነበር! ምንም ጊዜ ቢሆን፤ ኢትዮጵያ ልትፈርስ የምትችለው፤ የጀግኖች ልጆቿ ሬሳ ተረፍርፎ ካለቀ ባኋላ መሆኑ ባላንጣዎቿ ሊገነዘቡት ይገባቸው ነበር! ይኽን ታሪካዊ ሃቅ ለማስተዋል ግን አስተዋይ ኅሊና አልነበራቸውም።

“ዳመናው ሲደምን፤ ሲደማምን፤ ይውረዛል ገደል፤
“ይዘገያል እንጅ መመለሱ አይቀርም፤ የሠማዕት በደል።”

ተብሎ የተዜመው በከንቱ አልነበረም።  ሙሉውን ያንብቡ …