ሕብረ-ብሔራዊነት መለያችን፣ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቃችን

(ዴሞ ቅጽ 44 ቁ. 4 ሚያዚያ/ግንቦት 2011 ) – የኢሕአፓ አባላት እናት አገራቸው ኢትዮጵያን በዝናና በታሪክ ብቻ ሳይሆን በሥልጣኔም ሆነ በዕድገትዋ ከዓለም ቀደምት ሀገሮች ደረጃ ለማድረስ፤ የሚወዱትና የሚያከብሩትን ታላቅ ሕዝብ ከድኽነትና ከኋላቀርነት ለማላቀቅ እንዲሁም ፍትኅና እኩልነትን በሀገራቸው ለማስፈን ክቡር ዓላማና ብሩህ ተስፋን ሰንቀውም ነበር ለትግሉ የተነሱት፤ ወደ ትግሉም የገቡት። በአገር ሉዓላዊነትና በህዝባዊ ፍቅር ስሜትና እምነት መርህ ላይ ተሣሥረውና የተጠናከረ ሕብረ-ብሔራዊ ጥምረት ፈጥረው መሠረታዊ ለውጥን ለማምጣት የተሰለፉ ቆራጥ ጀገኖችም ነበሩ። ባጠቃላይም ከኢሕአፓ ውጪም ሆነ በኢሕአፓ ውስጥና በኢሕአፓ ዙሪያ ለየግል ጥቅማቸው ሳይሆን ላመኑባቸው ዓላማዎች በቅንነትና በቆራጥነት የተሰለፉት ታጋዮች በእርግጥም የመላው ሕዝብ ብርቅዬ ልጆች መሆናቸው ታሪክ የመሰከረላቸው ናቸው። ሙሉውን ያንብብቡ