“መሪ ከሞተ፤ አገር ተበተነ!” የአምባገነኖች ዝማሬ!

በፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ (መጋቢት 14 ቀን 2008 ዓ.ም.):  በሀገራችን የቅርብ ጊዜ የፖለቲካ ሥልጣን በጨበጡና ምህዳሩን በሚቆጣጠሩ ግለሰቦች አካባቢ ተደጋግሞ የሚሰራጭ ፕሮፓጋንዳ አለ።  ይኸውም፤ “እኛ ከሌለን ሀገሪቱ ትፈርሳለች።  ሕዝቧም ይበታተናል።  ሰማይ ምድሩ ይደበላለቃል።  የዓለም ፍፃሜ ይሆናል።” የሚል ሽብር መንዛት ነው። “ይህ ሁሉ መዓት ከሚመጣ፤ አሜን እያላቸሁ ተገዙ!” የሚል ከንቱ ማስፈራሪያን ያዘለ ፕሮፓጋንዳ ማሰራጨት ለዕድሜያቸው መቀጠያ ይረዳናል ብለው ይገምታሉ።  ቀደም ሲል በነበረው ታሪካችንም፤ ይህ ሁኔታ የሀገራችንን መፈረካከስ በሚመኙ ባዕዳን ጠላቶች ሳይቀር ተደጋግሞ ሲነገር እንደነበር፤ የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ።  ሙሉውን ያንብቡ…