ሰሞኑን በለገጣፎ ነዋሪዎች ላይ የተካሄደውን ዘረኛ የማፈናቀል አርምጃ አጥብቀን አናወግዛለን!

ከኢሕአፓ መግለጫ . . . ሰሞኑን በለገጣፎ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ለፍተው ደክመው ባፈሩት ገንዘብ የሰሯቸው ቤቶች በዘረኞቹ አመራር ትዕዛዝ ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ ፈርሶባቸዋል። ይኸው በዘውግ ተኮር ፖለቲካ ተጠራርቶ የተሰባሰበ የዘረኞች አመራር ለወሰደው እርምጃ የሰጠው ምክንያት ቦታው ለአረንጓዴ ፓርክ ይፈለጋል በሚል ሲሆን ፓርክ መሥራት የቀን ተቀን ኑሮውን ለመሸፈን የሚታገለውን ደሃ ነዋሪ ቤት ከማፍረስና ከህፃናት ትምህርት መጨናገፍ በልጦ እንደ ምክንያት መቅረቡ ብዙዎችን አስቆጥቷል። አዛውንት፣ ህሙማንና ህፃናት በተኙበት ቤታቸው ላያቸው ላይ ፈርሶባቸው ሜዳ ላይ ወድቀው ለረሃብ፣ ለቁርና ለአውሬ፣ ተጋልጠዋል። አዲሱ ሹም አስከብራለሁ የሚለው ያፈጠጠና ያገጠጠ “ሕገ መንግሥት” (ሕገ-አራዊት) ውጤቱ ሌላ ሳይሆን ይኸው ነው።
ከዛሬ 27 ዓመት በፊት በኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያዊያን ላይ ጦርነት የጀመሩት ወያኔዎች ሲሆን አሁን እያስቀጠሉ ያሉትም ወያኔዎች ናቸው። ኢህአዴግ/ወያኔ፤ ወያኔ/ኢህደግ። ስልቻ/ቀልቀሎ፣ ቀልቀሎ/ስልቻ እንዲሉ። እዚህ ላይ በመጫ ሙሉውን መግለጫ ያንብቡ . . .