ሳይጠሩት አቤት — የወያኔ ወዶ ገባ ምሁሮች ጉዳይ!


ከመላኩ ይስማው:  ኢትዮጵያዊነት እንዲህ በቀላሉ የማይጠፋ፣ የማይተን ሆኖ ነው እንጂ እስከዛሬም የተዋለበት ቀላል አይደለም። ወያኔ የሚያራምደውን የዘረኝነት ፖሊሲ ጦስ ምልክቶች እያየነው ነው – ያሳለፍናቸውን 23 ዓመታት ልብ ካልን። በረጅም ጊዜ ታሪክ፣ በፍቅርም በጦርነትም፣ በለቅሶም በሠርግም፣ በመውለድ በመግደልም በወዘተ ወዘተ የተገነባው ኢትዮጵያዊነት እየታገላቸው እንጂ፣ እየገዙን ያሉት የወያኔ መሪዎች ቅንጣትም ብሄራዊ ስሜት የላቸውም። ይህን ብሄራዊነት፣ ኢትዮጵያዊ ብሄራዊነት የሚያሳዩን ለአጭር ጊዜ ፕሮፓጋንዳ ጠቀሜታ ነው። አለዚያማ እስኪ ምን የፖሊሲ ማሻሻል አድርገዋል? ለአጭር ጊዜ ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ መግዛት፣ በረጅሙ ሌላውን አካባቢ በታትኖ እና የመተላለቂያ ቦንብ አሲዞ ማባላት፣ ራሷን የቻለች ታላቋን ትግራይም የመጨረሻው የማይታጠፍ ግብ አድርጎ መጓዝ ነበር ዓላማቸው፣ አሁንም ነው።   ታዲያ ለአጭር ጊዜ አቅጣጫ ማስቀየሪያ፣ ማዘናጊያ እንዲሆነው አስቦ፣ ምንም ይሁን ምን ቢሰራ፣ ሀገር የሚያፍራርስ ጠላት እንዴት ቸል ይባላል። ምነው ሶስቱ ምሁራን፣ ሶስቱ ? ? ? ሆናችሁ ሰውን ግራ አታጋቡ እንጂ!  ሙሉውን ጽሑፍ ያንብቡ…