ሴቶች የነፃነት መብታቸውን ሳይጎናፀፉ ማህበራዊ እድገት ሊኖር አይችልም!

ኢሕአፓ:  በተለያየ አሰያየሞች የሚጠራውና በየአመቱ የሚዘከረው ማርች 8 ቀን. 2015 (የካቲት 29 ቀን) አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዚሁ አመትም የሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት በሚኖሩበት የፖለቲካ ምህዳር ላይ የተመረኮዙ የተለያዩ ሴት ተኮር መሪ ቃሎችን በመንደፍ እየተከበረ ይገኛል። ይህ ለተለያዩ ቀናቶች የሚዘልቀው የበአል አከባበር የሚታወሰው መግለጫ በማውጣት፣ ”የት ነበርን? የት ደርሰናል? ምንስ ይቀረናል?” የተሰኙ ጥያቄዎችን ለመዳሰስ የውይይት ሴሚናር በማዘጋጀት፡ ጥናታዊና ትምህርታዊ ዘገባዎችን በማቅረብ እንደሆነም በተለያዩ የዜና ተቋማትና ድረገጾች እየወጡ ያሉ ዜናዎች ያመለክታሉ።  ሙሉውን ያንብቡ