የህዝብ ቁጣ አሁንም ከፍተኛ ነው፣ ከአሰብ ከተማ የተነሱ የኢምሬት የጦር አውሮፕላኖች የቀይ ባህር አፋር ተቃዋሚዎች ላይ ጥቃት አደረሱ

(ግንቦት 04 ቀን 2009 ዓ.ም) – የሕዝቡ ምሬትና ቁጭት ከፍተኛ መሆኑን በየቦታው የተዘዋወሩ የውጭ አገር ጋዜጠኞች አጋለጡ  – በሳኡዲ አረቢያ ያለፈቃድ የሚኖሩ ስደተኞች ቁጥር ግምት ከ200 ሺ ወደ 400 ሺ ከፍ ሲል የተመለሱት ከ23 ሺ አይበልጥም – በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኘው ቀበሮ ዘርማንዘሩ እንዳይጠፋ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገልጸ – ከአሰብ ከተማ የተነሱ የዩናይትድ አረብ ኤምሬት የጦር አይሮፕላኖች አፋር ውስጥ ተቃዋሚ ኃይሎች ላይ ጥቃት አደረሱ።

የወያኔ አገዛዝ በሕዝብ ላይ የጫነው አፋኙ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስለምና መረጋጋት አምጥቷል ብሎ ፕሮፓጋንዳ ቢነዛም በአንዳንድ ቦታዎች በአንዳንድ ቦታዎ ሰላም ያልሰፈነ መሆኑን እንዲሁም የሕዝቡ ቁጣ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን አንዳንድ የውጭ አገር ጋዘጠኞች የተለያዩ ቦታዎችን ጎብኝተው የጻፉት ዘገባ ይጠቁማል። በቅርቡ ጎጃምንና ጎንደርን ጎብኝቶ የተመለሰ አንድ ጋዜጠኛ አይሪሽ ታይምስ በተባለው ጋዜጣ ላይ ባሰፈረው ዘገባ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል አባላትን አነጋግሮ ሕዝቡ ያለውን ምሬትና ቅሬታ በጽሁፉ አስፍሯል። ለሰባት ዓመታት ያህል በወታደርነት ሲያገልግል የነበረ አንድ ጎልማሳ አነጋግሮ ወጣቱ ባሁኑ ወቅት ከወታደራነት የተሰናበተ መሆኑን የገለጸለትና ቀድሞውኑም ወደ ወታደርነት የገባው ሕዝብን ለማገልግል እንደነበር የገለጸለት መሆኑን ገልጾ ወታደር ሆኖ የራስን ሕዝብ መግደል የሽብር ወንጀል መሆኑን የገለጸለት መሆን ዘግቧል። ካነጋገራቸው ወገኖች የዴሞክራሲ ሥርዓትን ለማስፈን ጊዜ የሚወስድ ቢሆንም 25 ዓመት ሙሉ በአንድ አምባገነን አገዛዝ መሰቃየት ርግማን መሆኑንና በሁኔታው እንዲለውጥ ጸሎት እንዲሚያደርግ የነገረው መሆኑንም አስፍሯል። ጋዜጠኛው በማጠቃለያው ላይ አገዛዙ ሰላም አሰፈንኩ የሚለው በሺ የሚቆጠሩትን በማሰር በምርመራ በማሰቃየትና በመግደል መሆኑን ጠቅሶ በሕዝብ ላይ የሚታየው ብሶትና ምሬት ግን ዘላቂ ሰላም አንዳልተገኘ የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን በአንዳንድ ቦታዎ ላይ ለሚታዩት ትጥቃዊ እንድቅስቃሴዎች ምንጭ መሆኑንንም አብራርቷል።

በሳኡድ አረቢያ ያለፈቃድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ግምት ከሁለት መቶ ሺ ወደ አራት መቶ ሺ ያደገ ሲሆን እስካሁን የተመለሱት 23 ሺ ብቻ መሆናቸውን የወያኔ አገዛዝ ባለስልጣኖች ገልጸዋል። ይዘዋቸው በሚመጡት ዕቃዋዎች ላይ የሳኡዲም ሆነ የወያኔ አገዛዝ ቀረጥ እንደማያስከፍሏቸው በመግለጽ እንዲመለሱ በርካታ ውትወታና ጉትጎታ የተደረገ ቢሆንም እስካሁን የተመለሱት ቁጥር እንደተጠቀሰው አነስተኛ ብቻ መሆኑ ታውቋል። ምንም እንኳ በሳኡዲ መንግስት በኩል የተሰጠው የጊዜ ገደብ ካለፈ ስደተኞቹ ለእስር እና ከ 15 ሺ እስከ 50 ሺ ራያል (ከ 4000 እስከ 13 ሺ አምስት መቶ ዶላር) ቅጣት ለመክፈል እንደሚዳረጉ ያለሟቋረጥ እየተገለጽ ቢገኝም ስደተኞች ወደ አገራቸው ተመልሰው ከአፋኙና ከአምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ ስር ከመወደቅ ይልቅ እዚያው ሆነው ቢሞቱ የሚመርጡ መሆናቸውን በተደጋጋሚ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኘው ቀይ ቀለም ያለው ቀበሮ እየጠፋ መሆኑና መሆኑ ሲነገር የቆየ ሲሆን ቁጥሩን ለመጨመር ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተነገረ። በቁጥር 500 ብቻ የሆኑትና በባሌ በአርሲ በሰሜን ተራራና በወሎ ብቻ የሚኖሩት እነዚህ ቀበሮዎች ቁጥራቸው እንዲጨምር ቦርን ፍሪ በተባለው በዓለም የዱር ህይወት ድርጅት የሚረዳው የኢትዮጵያ ቀበሮ ጥበቃ ድርጅት የሚባለው ተቋም ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑ ታውቋል። ተቋሙ በአካባቢው የሚገኙትን ነዋሪዎች በማስተማር በሽታዎችን በመቆጣጠር ቁጥራቸውን ለመጨመር ከፍ ያለ ጥረት እያደረገ ነው ተብሏል።

ከአሰብ ከተማ የተነሱ የዩናይትድ አራብ ኢምሬት የጦር አውሮፕላኖች በኤርትራ ውስጥ በሚንቀሳቀሰውና የቀይ ባህር አፋር ዴሞክራቲክ ድርጅት በሚል ስም ጸረ ሻቢያ ሆኖ በሚንቀሳቀሰው ድርጅት ላይ ጥቃት የፈጸመ መሆኑን የድርጅቱ ቃል አቀባይ ለዜና ምንጮች ገልጿል። ቡድኑ በሰጥው መግለጫ አውሮፕላኖች ባካሄዱት ጥቃት አንድ ሰው የተገደለ ሲሆን ሌሎች ሰባት ሰዎች የቆሰሉ መሆናቸውን ጠቁሞ የአውሮፕላኑ ጥቃት በተደጋጋሚ የተደረገ መሆኑ አስርድቷል። የተባበሩት አረብ ኢሚሬት የአሰብን ወደ 500 ሚሊዮን ዶላር በመክፈል የተከራየ ሲሆን ዋና ዓላማ በከተማዋ ላይ የአየር ኃይል የጦር ሰፈር መስርቶ በየመን ሁቲ አማጽያን ላይ ጥቃት ለማደረስ መሆኑ ይታወቃል።

ከፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ዝርዝር ዜና ያንብቡ