ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ

ከአቶ ሰውየው (ሰሜን አሜሪካ):

ለያሬድ ጥበቡና መሰሎቹ ኢትዮጵያዊነትን ማዕከል ያደረገ የትግል ማዕበል እንደምታው ምን ሊሆን እንደሚችል ላልገባቸው። ለእንደኔ ዓይነቱ እነ ያሬድ ጥበቡ ኢሕአፓነታቸውን ያቆሙትና በቁመናቸው የሞቱት ያኔ ድርጅቱን ያፈረሱ መስሏቸው ፈርጥጠው ወያኔ ውስጥ ገብተው ወያኔ የሆኑ ጊዜ ሲሆን፤ አለፍ አለፍ ብለው ኢሕአፓ ነበርን ሲሉንም አያፍሩም። ለነሱ ኢሕአፓ ትግሉን ያቆመው ያኔ ነው ብለው ስለሚያምኑ ኢሕአፓ እነሱ ከሄዱ በኋላ እስከ ዛሬዋ ሰዓት እየተዋደቀ እንደሆነ አይናገሩም። ከወያኔና ከሻቢያ እንዲሁም ከሱዳንና ከአሜሪካ ጋር ሆነው ደርግ ከመውደቁ በፊት ኢሕአፓ ላይ የመዝመታቸውን የሚያሣፍር ታሪክ ሲናገሩም አንሰማም። እንደነ ፀጋዬ ደብተራው ያሉ ብርቅዬ ጓዶቻቸው ተይዘው በወያኔዎች ሲሰወሩና ውስጥ ለውስጥ ካለፍርድ ሲገድሉ ተባባሪዎች እንጂ ለአንዲት ደቂቃ እንኳን የደርግ ፋሺሽቶች ለፍርድ በሚቀርቡባት ኢትዮጵያ ደርግን አጥብቀው የታገሉ የኢሕአፓ ታጋዮች ለፍርድ እንኳ እንዴት አይቀርቡም ብለው መጠየቅ የተሳናቸው ማፈሪያዎች ናቸው። ሙሉውን ያንብቡ