በአገዛዙ ግፍ ቤንዚን በራሳቸው ላይ በማርከፍከፍ የሞቱ መምህራን ቁጥር ሁለት ደረሰ

በሰደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ:  ቅዳሜ ሚያዝያ 18 ቀን 2007ዓ.ም(April 25, 2015) በሀድያ ዞን በሶሮ ወረዳ በግንቢቹ ከተማ በሁመሮ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የፊዝክስ መምህር የነበረው ወንድሙ አብርሃም በወረዳው ም/ቤት የም/ቤቱ አባላት በስብሰባ ላይ በነበሩበት ወቅት በራሱ ላይ ቤንዚን በማርከፍከፍ ሕይወቱን አጥፍቷል። ለመምህሩ ሕይወቱን እንዲያጠፋ ምክንያት የሆነው የመድረክ ድርጅት አባል በመሆኑ ሩቅ ቦታ ተመድቦ ከነበረበት ት/ቤት ወደ ሌላ ቦታ ዝውውር ጠይቆ በመከልከሉና ከዚሁም ጋር ተያይዞ የሶስት ወር ደመወዙ ሳይከፈለው ስለቆየ ነበር። አቤቱታውን ወደሚመለከተው አካል ሄዶ ቢያመለክትም በከንቱ ከመመላለስ በስተቀር ጉዳዩን የሚሰማና ፍትህ የሚሰጥ አካል በመጥፋቱ ረሃብም ጊዜ የማይሰጥ በመሆኑ ራሱን ለማጥፋት ወሰነ። ቅዳሜ ሚያዝያ 18 ቀን 2007ዓ.ም ከወረዳው ም/ቤት ፊት ለፊት ተቃውሞውን ማሳያ የወያኔን ባንድራ በማውረድ በለበሰው ቱታ ልብስ ላይ ቤንዚን በማርከፍከፍ ክብርት ለኩሶ ደመወዙን ከልክለው ለችግር ያጋለጡትና ለጥያቄው መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ ያልነበሩት የም/ቤቱ አባላት ወደ ተሰበሰቡበት የስብሰባ አዳራሽ ለመግባት ቢሞክርም የተወሰኑት የም/ቤት አባላት የሰብሰባ አዳራሹን በር በመዝጋት የተወሰኑት መምህር ወንድሙን በዱላ ድብደበ ወደ ም/ቤቱ እንዳይገባ በማድረግና ሊያድኑትም ሳይሞክሩ በመቅረታቸው አካሉ ተለብልቦ ሕይወቱ አልፏል።መምህር ወንድሙ አብርሃም የተወለደው እዚያው በሶሮ ወረዳ ውስጥ በሸኖ ቀበሌ ነው።  ሙሉውን ያንብቡ