በኢሬቻ በዓል በዜጎች ላይ የደረሰውን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ኢሕአፓ ያወግዛል!

ከኃይል በመለስ አንዳችም ነገር የማይታየው ፋሽታዊውና ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ እሁድ መስከረም 22 ቀን 2009 ዓ.ም. በቢሾፍቱ/ደበረዘይት ከተማ በኦሮሞ ማኅበረስብ ወግና ባህል መሠረት የኢሬቻን ዓመታዊ በዓል ለማክበር በተሰበሰቡ ዜጎች ላይ ያካሄደው ሰብአዊነት የጎደለው ጭፍጨፋ በመቶ የሚቆጠሩ ዜጎች መገደላቸውና ቁጥራችው በውል ያልታወቀ መቁሰላቸው ተረጋግጧል። እስካሁን በህይወት መኖራቸውና አለመኖራቸው የማይታወቁም በርካታ ናቸው። ኢሕአፓ የወያኔ አገዛዝ ያደረሰውን ጭፍጨፋ አጥብቆ እያወገዘ ለሟች ወገኖችና ቤተሰቦች እንዲሁም የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ሁሉ የተሰማውን ልባዊ ሀዘን ይገልጻል። ሙሉውን መግለጫ ያንብቡ …