ባርነት የለመደ፤ በህልሙ ድንጋይ ይሸከማል

በፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ:  በተጨማሪም “የማንነት መሠረት ያጣ፤  በአጥር ውስጥ ይሸሸጋል” ተብሏል።  በኢትዮጵያዊነቱ ኮርቶ የኖረ/ የሚኖር ዜጋ ሁሉ፤  የማንነት ችግር ስለሌለው፤ መሸሸጊያ አያስፈልገውም።  የነፃነት ባለፀጋ በመሆኑም፤  ከባርነት ነፃ ለመውጣት ሲል፤ ድንጋይ ለመሸክም አይጎነበስም።  ዱሮውንም ቢሆን ነፃ ሕዝብ ነበርና! የጋራ ሽንፈትን ስለማይቀበልም፤ ለጋራ ድል ይታገላል እንጅ፤ የባዕዳንን ርዳታና ድጋፍ አይጠብቅም።  በራስ መተማመንን የሚተካው አለመኖሩን ስለሚገነዘብ፤ ከሕዝቡ፤ ከወገኑና ከትግል አጋሮቹ፤ ጋር ሆኖ፤ አምባገነኖችን እየታገለ ማንነቱን ከማስመሰከር በቀር፤ የሌሎቹን ይሁንታ አይጠይቅም።  አያሻውምም።  በጋራ ተባብሮ ጠላቶቹን ድል ይነሳል እንጅ፤ እየተበደለ በጋራ አያለቅስም።  በጋራ እያለቀሱ መኖር፤ ውርደት ስለሚመስለው፤ ለጋራ ድል ተባብሮ ይታገላል!  ደሙን እያፈሰሰም የወገኖቹን እምባ ያደርቃል።  የሕዝቡን የነፃነት ጥማት ለማርካት ይታገላል።  ይሰዋል።   ሙሉውን ያንብቡ . . .