‘’ባዶ!’’ አለ ገሞራው

ከጌትነት

ያ ትልቁ ጠቢብ፣ ገሞራው እንዳለን፣
ዜሮ ቁጥር ላይሆን፣ በከንቱ መማሰን!
ቢቃጠል ሆቴሉ!
ቢነቀል ሐውልቱ!
ቢነድ ደን ቅጠሉ!
የቼብሃ ዛፍ ነው፣ ሁሉም መሠረቱ፣
አይቀርም ሐቅ ነው፣ ዳግመኛ መምጣቱ!
ሲጠፉ አጥፊዎቹ! እሱ መታየቱ!
ደምም ቢንቆረቆር!
አጥንት ቢሰባበር!
ስጋ በጭካኔ ቢከተፍ! ቢመተር!
ይህ ሁሉ ህያው ነው፣ ቆሞ እሚያኖር ሀገር!
ሙሉውን ግጥም ያንብቡ …