ተቃውሞው ተቀናጅቶ የወያኔን ውድቀት ያፋጥን

(ኢሕአፓ)  – የፍርሃትንና የልዩነትን ግንብ አፍርሶ በተለያየ የአገራችን ክፍል ያለው ሕዝብ በትግሉ መድረክ አለና ካለ ጀምሮ ወያኔ ባለው የአፈና አቅም EPRPሁሉ ሺዎችን ገድሎ፤ ብዙዎችን አግቶና ለስየል ዳርጎ ትግሉን ሊያፍን ቢሞክርም የሕዝብ አመጽ ቀጥሎና ግሎ ወያኔን እያርበደበደ መሆኑ እየታየ ነው።  የወያኔ የውድቀት ደወል ተደውሎ ደወሉም በሀገራችን በሞላ እየተደመጠ ነው።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በየአቅጣጫው በተለያዩ ከተሞች ሕዝብ ጸረ ወያኔ ሰልፍና ትግልን እያፋፋመ ባለበት ወያኔ በሚችለው የማደናገሪያ ሙከራ ሁሉ ተሰማርቶ ክፍፍልን በማፋፋም፤ ስልጣን ልንለቅ ነው ብሎ ቧልትን በማሰራጨት፤ ግድያውን ሳይታክት በማካሄድ፤ ቅጥረኞቹን በሀገር ቤትም በውጭም በማሰማራት፤ ወዘተ በስልጣን ሊቀጥል እየጣረ ነው።  የስውርና የይፋ ቅጥረኞቹም በጥረቱ ተካፋይ ሆነው የሀገር ወዳዶችን ትግል ለማደናቀፍ በየፊናቸው እየዘመቱ ናቸው።  ሙሉውን መግለጫ ያንብቡ . . .