ተንበርክኮ ከመኖር በዓላማ ፀንቶ መሞት ይሻላል!!

በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ ዝነኛው ገጣሚና መምህር ኃይሉ ገብረዮሐንስ በስደት ከሚኖርበት አገር ስዊድን( ስቶኮልም ከተማ) ጥቅምት መጨረሻ 2007 ዓ.ም ማረፉን የሰማው በከፍተኛ ሀዘን ነው። ሃይሉ ገብረዮሐንስ በመምህርነት ሙያው እንደ አንድ ሃላፊነት የሚሰማው ዜጋ ሀገር ወዳድ ትውልድ ለመፍጠር የበኩሉን አስተዋፅኦ አድርጓል። የዚያ ትውልድ ግንባር ቀደም የለውጥ ሃዋሪያ ሰለሆነም የአገር ባለውለታ ነው። በተፈጥሮ ባገኘው ተሰጥኦና በትምህርት ባዳበረው ገጣሚነት ቀስቃሽ ፣አነቃቂ፣ ትምህርታዊ፣ ፍልስፍናዊና ሥነ ጥበባዊ የሆኑ ግጥሞችን በማቅረብ ይታወቃል።  ሙሉውን መግለጫ ያንብቡ …