ቶኩማ (ሶኑማ)

ከባላንገብ ሚካኤል – አብይ አህመድ በወያኔ ብብት ዉስጥ ያደገ ብቻ ሳይሆን ከሃያ አመታት በላይ ከነርሱ ጋር ሰምሮ እና አብሮ በንፁሃን ዜጎች ላይ በተፈፀመዉ ወንጀል ሁሉ ሴሰኞ ከሆነዉ ከደብረፂዮን ባልተናነሠ መንገድ የተሳተፈ እና መጠየቅ ያለበት የወያኔ ሹም እንጅ የህዝብ ተወካይ አልነበረምም አይደለምም።  አብይ ከሌሎቹ ወያኔወች እና የወያኔ ባለሞሎች የተለየ አልነበረም አይሆንምም። ስለዚህ አብይ ለየት ያለ የአነጋገር ዘይቤ ያለዉ ያዉ ወያኔ ነዉ (ቶኩማ/ሶኑማ)። በመሆኑም እነ መለስን እና ሌሎች ሟች ወያኔወችን ከማድነቅ የተለየ ቃል ሊወጣዉ አይችልም አልቻለምም። ቢሆንማ ትግራይ የኢህአፓ ጀግኖች እነ ዶር ተስፋዮ ደበሳይ እና ጋይም ገብረእግዚአብሄር (ምሃል አዲስ አበባ ላይ የወያኔን ጀስታፖ ፊት ለፊት ገጥሞ ጥሎ የወደቀዉን እና ያልተዘመረለትን አብሪ ኰከብ) እንዲሁም  የሌሎች ስመጥር ጀግኖች የትዉልድ ቦታ መሆኑን ይጠቅስ ነበር። ይልቁንም ወያኔ አጣብቂኝ ዉስጥ ሲገባ ለችግር ማስታገሻነት ይረዳዉ ዘንድ ለዓመታት ጠፍጥፎ ከሠራቸወ የማደናገሪያ መሣሪያወቹ ዉስጥ አንዱ ነወ።

ትግርኞ ተናገረ ከረባታዉ አማረ ብለዉ ሸብረክ ለማለት እየዳዱ ያሉ ተቃዋሚ በሉን ባዮች ድሮም ከወያኔ ለመተቃቀፍ ምክንያት ሲፈልጉ የነበሩ ናቸዉ እና መንገዱን ጨርቅ ያድርግላቸዉ። የሃገራችን መሠረታዊ የፓለቲካ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በአንድ መሪ የንግግር ክህሎት እና የትምህርት ደረጃ ብቻ የሚፈታ የሚመስላቸዉ የዋሆች ቁጥራቸዉ ተበራክቶ ሲታይ እና መነሻ የሆነ የዴሞክሪያሲያዊ ስርዓት መደላድሎችን ለማረዳት የተሳናቸዉን የስም ተቃዋሚወች ማስተዋሉ በርግጥ ያማል። ወያኔ የሚመራዉ እኩይ ቡድን መዋቅራዊ ቅርፅ እና ይዘት ያለዉ ስብስብ ሆኖ ሳለ አንድ እነኝህን መዋቅሮች በአግባቡ እንዳይጠቅማበቸዉ ተደርጎ የተቀመጠን ጡንቻ ቢስ ሠዉ ኤልሻዳይም ሙሴም ማለት እብደት ካልሆነ ምን ሊባል ይችላል?

ሲጀመር የህዝብ ጥያቄ ሃይለማሪያምን በአብይ መተካት አልነበረም አይደለምም።  የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ ዘረኞ በሆነዉ እና ከራሱ ቡድን በላይ በማያስበዉ የወያኔ ቡድን መቃብር ላይ ዜጎች በእኩልነት የሚኖሩባትን ዴሞክሪያሲያዊት አንድ ኢትዮጵያን መመስረት ነዉ። የትግራዮ ወያኔ መለሠ ዜናዊ እና የወላይታዉ ወያኔ ሃይለማሪያም ስልጣን ላይ እያሉ ያዙኝ ልቀቁኝ የሚያበዙት የሳይበር አርበኞች አንድም ቦታ ላይ በተግባር ሳይፈተን የኦሮሞ ወያኔ ነዉ አሁን የሚመራዉ ብለዉ የምላስ ሰይፋቸዉን ወደ ካፎቱ መመለሳቸዉ ያስደምማል ያስቃልም። ወያኔን የምንቃወመዉ ለህዝብ ያልበጀ እና የማይበጅ ስርዓት በመሆኑ እንጅ መሪወቹ የመጡበትን የዘር ሃረግ መርጠን አለመሆኑ ሊሠመርበት ይገባል። ወያኔ አስመሠለም አላስመሠለ አመነም አላመነ ኢትዮጵያዊነት እያቸነፈ ነዉ ያቸንፋልም።

ወያኔ ጨርቅ ብሎ የተሳለቀባት ጀግኖቹ አባቶቻችን የተሠዉላት ምንም ያልታከለባት አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሠንደቅ አላማችን አራት ኪሎ ላይ በኩራት ትዉለበለባለች።  የመቶ ሚሊዮን ሃገር የሆነችዉን ታሪካዊ ሃገራችን የኢትዮጵያ ህዝብ ዉክልና ሳይኖራቸዉ የባህር በር ያሳጦትን በሃገር ክህደት ወንጀል እንፋረዳቸዋለን። በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን ጨምሮ በእስር ያንገላቱ እና የገደሉ የወያኔ ባለስልጣናት ለፍርድ ይቀርባሉ። ኢትዮጵያ ዜጎች በነፃነት ሃሳባቸዉን የሚገልፁባት እና የሚደራጁበት ሃገር ትሆናለች። ካለብቃታቸዉ በወታደራዊ ማዕረግ ትክሻቸዉ የጎበጠ ምሃይም የወያኔ ወታደራዊ ሹማምንት ይራገፉ እና የመከላከያ ሠራዊቱ ኢትዮጵያዊ ይሆናል። የፓሊስ እና የፀጥታ ሃይሎች ህግ አስከባሪ ብቻ ይሆናሉ። ፍርድ ቤቶች በነፃነት የህግ የበላይነትን ያስከብራሉ። ዜጎች በሙያዊ ብቃታቸዉ ብቻ የስራ ዘርፍ ላይ ይደለደላሉ። በዝርፊያ የከበሩ የወያኔ ሹማምንት ንብረታቸዉ ተወርሶ ለፍርድ ይቀርባሉ። የኢትዮጵያ ኤምባሲወች እና የቆንስላ ጵህፈት ቤቶች የወያኔ ህገወጥ የዕፅ ንግድ ማዘዋወሪያ ከመሆን ወጥተዉ ኢትዮጵያዉያን በሚኖሩበት ቦታ ሁሉ መብታቸዉ ይጠበቅ ዘንድ ሙሉ አገልግሎት ይሠጣሉ። እነኝህ እና ሌሎቹ ጥያቄወች መልስ እስኪያገኙ እና ህዝባዊ መንግስት እስከሚመሠረት ድረስ ትግሉ ይቀጥላል። እናቸንፋለንም።