ነግበኔን እናስብ፣ በተናጠል እንዳንጠቃ እንተባበር

በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ፡  ወያኔ በስልጣን ላይ በተቀመጠ ማግስት በአባላቱ ፍላጎትና ነፃ ተሳትፎ በዴሞክራሲያዊ አካሄድ የተደራጀውን ሕጋዊ የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር (ኢመማ) ዕውቅና ሻረ።  የአመራር አባላቱን በመግደል፣ በማሰር፣ አፍኖ በመሰወርና ከሥራ በማናፈቀል፣ ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ የአባላቱን ገንዘብ ከባንክ በመዝረፍ፣ የክልልና የዞንና ማዕከላዊ (አገር አቀፍ) ጽ/ቤቶችን በመውረር፣ በመውረስና በመመዝበር የሻዕቢያ ወኪል ለነበረው በዮሐንስ ሐጎስ ለሚመራው ተለጣፊ ቡድን እንዳስረከበ ይታወሳል።

ታሪክ እራሱን ይደግማል እንዲሉ ሆነና ጥር 21 ቀን 2007 ዓ. ም. ወያኔ ሰራሹ ምርጫ ቦርድ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) እና መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅትን (መኢአድ) ወያኔ በፓርቲዎቹ ውስጥ አስርጎ ላስገባቸው ቅጥረኞች ለትዕስቱ አወልና ለእነ አበባው መሐሪ ዕውቅና መስጠቱ ሥርዓቱ ጸረ ነፃ ድርጅትና ጸረ-መድብለ ፓርቲ እና ጸረ-ዴሞክራሲ እንደሆነ በገሃድ ያስመሰከረበት ሁኔታ ነው።  ሙሉውን መግለጫ ያንብቡ …