አርአያው ምሑር ዶክተር መስፍን አርአያ አርፏል (ከግንቦት 1944 — የካቲት 2015)

Dr Mesfin Araya
Dr. Mesfin Araya (1944 – 2015)

ሀገር ወዳዱና ለአያሌዎች አርአያ የነበረው ዶክተር መስፍን አርአያ በማለፉ ኢሕአፓ የተሰማውን መሪር ሐዘን በዚህ መልዕክት አማካይነት እየገለጸ ቤተሰቡና ወዳጆቹ ሁሉ እንዲጽናኑ መልዕክቱን ያስተላልፋል።  ዶክተር መስፍን አርአያ በአካለጉዛይ ኤርትራ ተወልዶ በልጅነቱ ዕድሜ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ  ትምህርቱን በምኒሊክ  ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጨርሷል። በዚያን  ወቅት ቀኃስ ዪኒቨርስቲ  በአሁኑ ወቅት ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ  ገብቶ በፖለቲካል ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል። ዶ/ር መስፍን በኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴ መሉ ተሳትፎ የነበረውና በምስጢራዊ እንቅስቃሴዎች በአስተማማኝነት የተሳተፈ ጽኑ ኢትዮጵያዊ ነበር።  ሙሉውን ያንብቡ