አሮጌው 2007 ዓ.ም. ተገባዶ አዲሱ ሲተካ! የት ላይ ነን? ምንስ ይጠብቀናል?

ዴሞ (የኢሕአፓ ልሳን): በሀገራችን የዘመን አቆጣጠር መሠረት ሕዝባችን 2007 ዓ.ም. ዘመነ ሉቃስን አሳልፎ ወደ አዲሱ 2008 ዓ.ም. ዘመነ ዮሃንስ ከተሸጋገረ ጥቂት ቀኖችን አሳልፏል።  የሰው ፍጡር በህይወት እስከኖረ ድረስ ማንኛውም ዜጋ እንደ አቅሙና ችሎታው፤ መድረስ ከሚፈልገው ሁለንተናዊ የኑሮ መሻሻል አንፃር ባለፈው ዓመት በክፉም ሆነ በደጉ የተጓዘባቸውን ሂደቶች፣ በቀን ተቀን ሕይወቱ ያጋጠሙትን ችግሮች በሕሊናው እያሰላሰለና እየመረመረ ለመጪው ወራት ለራሱም ሆነ ለቤተሰቡ እንዲሁም ከፍ ሲል ለሀገሩና ለወገኖቹ መልካም ምኞቱን መግለጽ ብቻ ሳይሆን ምን ማድረግ እንዳለበትም እቅዱን እያለመ አዲሱን ዓመት በተቻለው መጠን እንዳመጣጡ ለመቀበል መንቀሳቀሱ የሚጠበቅ ነው::  ሙሉውን ያንብቡ