ኢሕአፓ በጀግናው አርበኛ በኮሎኔል አስናቀ ዕንግዳ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በቁጭት ይገልፃል!

ኮሎኔል አስናቀ ዕንግዳ መላ ዕድሜያቸውን ያሳለፉት፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነት፤ ፍትኅ-ርትዕ፤ ዴሞክራሲ ሥርዓትና ለሀገር ልዋላዊነት ሲታገሉ ነው። በዚኽም ምክንያት የአያሌ ዓመታት እስርና መንገላታት፤ ስደትና ጉስቁልና ተፈራርቀውባቸውል። ይኽንንም በፀጋ ተቀብለው፤ በመርኅ ላይ የተመሰረተ ትግል ሲያካሂዱ በመኖራቸው፤ አርአያነተቸው ለዚያ ሰማዕታዊ ትውልድ አንፀባራዊ ኮከብ ሆኖ ቆይቷል። ወደፊትም በታሪክ እየተጠቀሰ የሚኖር ነው።

ሦስቱን ተፋራራቂ አምባገነን ሥርዓቶች፤ በግንባር ቀደም ሲታገሉ መኖራቸው፤ የትግል ፅናታቸው እንከን የማየወጣው መሆኑን በተግባር አስመስክረዋል። በተለይ በደርግ ዘመን ኢሕአፓ ነጻ ባወጣው አካባቢ በኢሕአፓ አባልነታቸው ታጋዮችንና አገር ወዳዶችን በማሰባሰብና ለትግል በማነሳሳት ከፍተኛ ጀብዱ ፈጽመዋል። የወያኔ አገዛዝ በሥልጣን ሲሰየምና የአገራችን ህልውና አደጋ ላይ ሲወድቅ ከፋፋዩንና አምባገነኑን ሥርዓቱ በብርቱ የተቃወሙ ሲሆን ታጋይ ድርጅቶችን በማስተባበር፤ በመምከርና በማበረታት የተጫወቱት ግምባር ቀደም ሚና የሚረሳ አይደለም። በዚኽም እንኮራባቸዋለን። እንወዳቸዋለን። እናመሰግናቸዋለን። ሙሉውን  መግለጫ ያንብቡ