ኢሕአፓ ወያኔ በቅርቡ በጎንደር ክፍለ ሀገር በሕዝብ ላይ ያደረገውን ጭፍጨፋ ያወግዛል

ባለፈው ሳምንት የወያኔ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከባድ መሳሪያዎች በመታጀብ ጎንደር አርማጭሆ ውስጥ ሶረቃ በሚባለው አካባቢው አርሶ አደሮችን በኃይልና በማን አለብኝነት አስነስተው ቦታውን ወደ ትግራይ ክልል ለማጠቃለል ያደረጉት ጥረት ሕዝቡ ከዳር እስከዳር በመንቀሳቀስና ውጊያ በመግጠም ያከሸፈው መሆኑ ታውቋል። በተደረገው ግጭትም ከሁለቱም በኩል ጉዳት የደረሰ መሆኑ ከሥፍራው የሚገኙ ዜናዎች ያስረዳሉ። ሁኔታው እስካሁን ያልበረደ ሲሆን ሕዝቡም ከዳር እስከ ዳር ተጠራርቶ መብቱን ለማስከበርና ንብረቱን ለማስጠበቅ ባንድነት ለመታገል ወስኗል።  ሙሉውን ያንብቡ…