ኢትዮጵያ: ለልጆቿ የተከለከለች ፍሬ

የፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሀተታ: ዕምቅና ተጨባጭ የሆነው የተፈጥሮ ሀብቷ ሞልቶ ተርፎ፤ ዜጎቿን መመገብ ያልቻለች ምድር ሀገራችን ኢትዮጵያ መሆኗ እስከ ዛሬ ደረስ ያልተገነዘበ ፍጡር ይኖራል ብለን አንገምትም።  እኛም ዛሬ ይህንን ለማውሳት የፈለግነው፤ ለድኅነታችን፤ ለችግራችንና ለረሀብ ጥማታችን ማስተዋወቂያ አዲስ ሰሌዳ ለመዘርጋት አይደለም።  ብሄራዊ ችግሮቻችንን በአደባባይ ማውጣቱም ሀዘንን እንጅ፤ ደስታን፤  ሀፍረትን እንጅ ኩራትን እንደማያመጣልን ደህና አድርገን እንገነዘባለን።  ዘለዓለም ስለ ሀገራችን መከራና ችግር ብቻ እያወሳን ማነብነብ አንዳችም መፍትሄ እደማያስገኝ እንረዳለን።   ሙሉውን ያንብቡ …