እንደ ጨጓራ የፖለቲካ ሽንፍላም ቢያጥቡት አይጠራም


ማርቆስ ደጀን: 
ለወያኔ በስልጣን መክረም በጣም ከጠቀሙት ክስተቶች አንዱ የፖለቲካውን መድረክ በሽንፍላ ቅጥረኞችና ከፋፋዮች ሊያጨናንቅ መቻሉ መሆኑ ያድባባይ ምሥጢር ነው።  እኛም  “ብልጥን እባብ አንድ ጊዜ ይነክሰው ይሆናል፤ ሞኝን ግን ሁለት ጊዜ – አንድም ሳያየው፣ ሁለተኛም ከዚህ ጋር የነደፈኝ ብሎ ሲያሳይ"  እሚለውን ይትብሃል ልብ ማለት ተስኖን እየተጃጃልን ተመችተንለታል።  ድንግርግርና ውዥንብር በሰፈነ መጠን የተቃዋሚዎቹ ጎራ ይፈረካከሳል፤ ከስህተታችን በመማር ፈንታ በስህተታችን ተስፋ ቆርጠንም፣ ወደ ተስፋ አስቆራጮቹ አምባ የእርድ በሬ ሆነን የምንሄድ አለን።   ወደ ዝርዝሩ ገብቼ አካፋን አካፋ ከማለቴ በፊት ግን በቅድሚያ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ይህን የወያኔን ተንኮል እያገዙ ያሉትን ክፍሎች መጠቆሙና መውቀሱ ተገቢ ይመስለኛል።  የሹም ዶሮ ነን ለምንስ ተነክተን እሽ ተብለን አይሉም ብዬ በመገመት፤ መደማመጡ፣ ስህተትን መመለካከቱ ለጋራ ጥቅም ነውና።  ሙሉውን ጽሑፍ ያንብቡ…