ኦባማ ምን አጠፋ?

ከሀማ ቱማ: የዛሬ ስንት ዓመት ባራክ ኦባማ አሜሪካዊ ሳይሆን ኬንያዊ፤ አፍሪካዊ፤ ጥቁርም የመሰላቸው ጥቂቶች አልነበሩም። ግለሰቡ አሜሪካዊና ለሀገሩ ጥቅም ብቻ የሚቆም መሆኑንም በተመለከተ ብዥታ ሰፍኖ ነበር ማለት ይቻላል። ሀገራቸውን የረሱ እንበልና ስንት ኢትዮጵያውያን የነበሩ ሁሉ ለኦባማ ገንዘብ ሰበሰቡ፤ ሲመረጥም ፈነደቁ፤ አንዳንዶቹማ ኦባማ ስለዴሞክራሲ የለፈፈውን አምነው፤ ፖለቲከኛ መሆኑን ረስተው፤ ለአሜሪካ ጥቅም የቆመ መሆኑ ዘንግተው ወያኔ አለቀላት ሲሉም ተደምጠዋል። ማለቅ የጀመረው የራሳቸው የተሳሳተ ድምዳሜ ሆኖ ሳለ። የአሜሪካ ብሔራዊ ጥቅም ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ጋር ተጻሮና ተፋጦ ከቆየ ዘመን ያለፈ ቢሆንም ታሪክን ማወቅና መረዳት ያቃታቸው ክፍሎች ይህን ሀገር የኢትዮጵያ ወዳጅ አድርገው ለመፈረጅ ሁሌም ደፋ ቀና ሲሉ ማየት ምጸታችን ከሆነም እንዲሁ ዘመን አልፏል። ኦባማ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሳይሆን ባለው ሀላፊነት የአሜሪካ ቡችላና መጋዣ ለሆነ ወያኔ ጥብቅና የሚቆም መሆኑን መገመት ባላዳገተ ነበር። ለወያኔ ስልጣን መያዝና ለተከተለው የኤርትራ መገንጠል ዋናው ደጀን/ረዳት አሜሪካ ካልነበረ ማን ሌላ ሊወቀስ ነው! አሜሪካንን በሚገባው ቋንቋ ማነጋጋር ሲገባ (ይህን ትምህርት ደግሞ ሞቃዲሾም ቤይሩትም ብሎ መማር ይቻል ነበር) አትርሱን፤ እዘኑልን፤ ፕሊስ ፕሊስ ማለቱና መለመኑ ስለበዛ መናቅ መከተሉ የሚጠበቅ ነበር::  አሜሪካም ወያኔን ስትደግፍ ህዝብን ግን ንቃለች፤ አሁንም የተለወጠ የለም። ኦባማ ደግሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት እንደመሆኑ የአሜሪካን ጥቅም ማስቀደሙ የሚጠብቅ ነውና 90 ሚሊዮን ድሀ ደንታ ሊኖረው አይችልም። የለውምም።   ሙሉውን ያንብቡ