ከርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የወቅቱን የሃገራችን ኢትዮጵያ ሁኔታ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

. . .  ቤተ ክርስቲያናችን ካለፉት ወራቶች ጀምሮ በኦሮሚያ፤ በጎንደርና በጎጃም፤ እንዲሁም በሌላ የሃገሪቱ ክልሎች አገዛዙ እስከ አፍንጫው የታጠቀ ወታደራዊ ኃይልን ባልታጠቀ ሰላማዊ ሕዝብ ላይ በማዝመት በንጹሐን ዜጎች ላይ የሚያደርሰውን ግድያ ከማውገዝ በተጓዳኝ ለእነዚሁ ህይወታቸውን በግፍ ለተነጠቁ ኢትዮጵያውያን በየጊዜው የጸሎት መርሃ ግብር በማካሄድ ላይ የምትገኝ ሲሆን ይህን በኢትዮጵያ ሃገራችን ውስጥ በመካሄድ ላይ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት፤ አረመኔያዊ ግድያና ጭፍጨፋ በመላው ዓለም የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በአንድነት ያወግዙትና ይኮንኑት ዘንድ ጥሪዋን ታስተላልፋለች።  ሙሉውን መግለጫ ያንብቡ . . .